2 ሳሙኤል 22:19-51
2 ሳሙኤል 22:19-51 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ። ወደ ሰፊ ቦታ አወጣኝ፤ በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕናም ይመልስልኛል። እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትያለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም። የእግዚአብሔርን ሕጎች ሁሉ እፈጽማለሁ፤ ሥርዓቱንም ከማክበር ወደ ኋላ አላልኩም። በእርሱ ዘንድ ንጹሕ ነበርኩ፥ ከኃጢአትም ራሴን ጠብቄአለሁ፤ እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና ዋጋዬን ከፈለኝ። አምላክ ሆይ! ለአንተ ታማኞች ለሆኑት ታማኝ ነህ፤ እውነተኞች ለሆኑትም እውነተኛ ነህ። ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፤ ለጠማሞች ግን ተገቢ ዋጋቸውን ትሰጣለህ። ትሑቶችን ታድናለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ታዋርዳለህ። እግዚአብሔር ሆይ! ለእኔ ብርሃኔ ነህ፤ አንተ አምላኬ ጨለማዬን ታበራለህ። በአንተ ርዳታ አንድ የጦር ጓድ አጠቃለሁ፤ አንተ አምላኬም ቅጥሩን ለመዝለል ትረዳኛለህ። የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም ነው፤ ቃሉ የጠራ ነው፤ እርሱን መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ማን ነው አምላክ? ከእርሱስ በቀር መጠጊያ የሚሆን ማነው? ብርታትን የሚሰጠኝና መንገዴን የሚያቃናልኝ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያጠነክራል፤ በከፍታ ቦታዎችም ያለ ሥጋት ለመቆም ያስችለኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ የነሐስን ቀስት መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል። አምላኬ ሆይ! የማዳን ጋሻህ ሰጠኸኝ፤ የአንተ ኀይልም ያጸናኛል። አረማመዴን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም፤ ዳግመኛ እንዳይነሡ አድርጌ እመታቸዋለሁ፤ በእግሬም ሥር ይወድቃሉ። ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ። ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ፤ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ። የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ አደቀቅኋቸው፤ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም እረግጣቸዋለሁ። ከዐመፀኛ ሕዝብ አዳንከኝ፤ በአሕዛብም ላይ ሾምከኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ይገዛልኛል። ባዕዳን ያጐነብሱልኛል፤ ዝናዬን እንደ ሰሙም ይገዙልኛል በፍርሃት ይጨነቃሉ፤ በመንቀጥቀጥም ከምሽጋቸው ወጥተው ወደ እኔ ይመጣሉ። እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል! እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችንም ከበታቼ አድርጎ ያስገዛልኛል። ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ። ጌታ ሆይ! ስለዚህ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ። እርሱ ላነገሠው ንጉሥ ድልን ያጐናጽፈዋል፤ እርሱ ከቀባውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳየዋል፤ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘለዓለም ይህን ያደርጋል።
2 ሳሙኤል 22:19-51 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ። ወደ ሰፊ ስፍራ አወጣኝ፤ ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ። “እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤ እንደ እጄም ንጽሕና ከፈለኝ፤ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም። ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም። በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም፤ ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣ በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ። “ለታማኝ ሰው ታማኝ መሆንህን፣ ለፍጹም ሰው ፍጹም መሆንህን ታሳያለህ። ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ። አንተ ትሑታንን ታድናለህ፤ ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል። በአንተ ጕልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ፤ በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ። “የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው? ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው። እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ። የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል። ርምጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተሰነካከሉም። “ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤ እስኪጠፉም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም። ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል። ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣ ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከክሃቸው። ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው። ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው። ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አደቀቅኋቸው፤ በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም። “በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ። የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ፤ የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል። ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ። “እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን! አምላኬ የድነቴ ዐለት ከፍ ከፍ ይበል። በቀሌን የሚመልስልኝ፣ አሕዛብንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል። አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ። “ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣ ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል።”
2 ሳሙኤል 22:19-51 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ። ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፥ ወድዶኛልና አዳነኝ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፥ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል፥ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁምና። ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ከሥርዓቱም አልራቅሁምና። በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ። እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ። ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፥ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፥ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ። አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ። አቤቱ፥ አንተ መብራቴ ነህና፥ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል። በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፥ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና። የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው። ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው? ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቃና፥ እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያረታ፥ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው። እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴ የናስ ቀስት እገትራለሁ። የማዳንህንም ጋሻ ሰጠኸኝ፥ ተግሣጽህም አሳደገኝ። አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ፥ አጠፋቸውማለሁ፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። ጮኹ፥ የሚረዳቸውም አልነበረም፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ አልሰማቸውምም። እንደ ምድር ትቢያ ፈጨኋቸው፥ እንደ አደባባይም ጭቃ ረገጥኋቸው፥ ደቀደቅኋቸውም። ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል። የባዕድ ልጆች ደለሉኝ፥ በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ። የባዕድ ልጆች እየጠፉ ይሄዳሉ፥ ከተዘጉ ስፍሮች እየተንቀጠቁ ይወጣሉ። እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ ጠባቂዬም፥ ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴ ጠባቂ አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል፥ በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ፥ አሕዛብን በበታቼ የሚያስገዛ፥ ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፥ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ። አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ። የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው፥ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል።
2 ሳሙኤል 22:19-51 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደጋፊዬ ሆነ። ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕናም ይመልስልኛል፤ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁምና። ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበርና፤ ጽድቁም ከእኔ አልራቀምና። በእርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆናለሁ፤ ከዐመፃዬም ራሴን እጠብቃለሁ። እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዐይኖቹ ፊት መለሰልኝ። ከጻድቅ ጋር ጻድቅ ትሆናለህ፤ ከንጹሕ ሰውም ጋር ንጹሕ ትሆናለህ፤ ከተመረጠም ጋር የተመረጠ ትሆናለህ፤ ከጠማማ ጋርም ጠማማ ትሆናለህ። አንተ የተዋረደውን ሕዝብ ታድናለህና፤ የትዕቢተኞችን ዐይኖች ግን ታዋርዳለህ። አቤቱ! አንተ መብራቴ ነህና፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራልኛልና። በአንተ ብቻዬን እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና። የኀያል አምላክ መንገድ ንጹሕ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤ በእሳትም የጋለ ነው፤ በእርሱም ለሚታመኑት ጠባቂያቸው ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ጽኑዕ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር ፈጣሪ ማን ነው? በኀይል የሚያጸናኝ ኀያል እርሱ ነው፤ መንገዴንም ንጹሕ አድርጎ አዘጋጀ፤ እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች አጸና፤ በኮረብቶችም አቆመኝ። ለእጆቼ ጦርነትን ያስተምራል፤ ለክንዴም የናስ ቀስት አዘዘ። የመድኀኒቴንም ጋሻ ሰጠኸኝ፤ መልስህም አበዛችኝ፤ በሜዳም አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ፤ አጠፋቸውማለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። እቀጠቅጣቸዋለሁ፤ መቆምም አይችሉም፤ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። በጦርነትም ጊዜ በኀይል ታጸናኛለህ፤ በላዬ የቆሙትንም በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፤ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። ጮኹ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ አልሰማቸውምም። በነፋስ ፊት እንዳለ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨኋቸው፤ እንደ ጎዳናም ጭቃ ረገጥኋቸው፤ ደቀደቅኋቸውም። ከአሕዛብ ጠብ አድነኝ፤ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፤ የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ። የባዕድ ልጆች ዋሹኝ፤ በጆሮ ሰምተው መለሱልኝ። የባዕድ ልጆች አረጁ፤ ከማንከሳቸውም የተነሣ ተሰናከሉ። እግዚአብሔር ሕያው ነው፤ ጠባቂዬም ቡሩክ ነው፤ የሕይወቴ ጠባቂ አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል፤ በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ ጽኑዕ ነው። አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል፤ ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኛም ሰው ታድነኛለህ። አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ። የንጉሡን መድኀኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘለዓለም ያደርጋል።”
2 ሳሙኤል 22:19-51 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ። ወደ ሰፊ ስፍራ አወጣኝ፤ ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ። “እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤ እንደ እጄም ንጽሕና ከፈለኝ፤ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም። ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም። በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም፤ ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣ በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ። “ለታማኝ ሰው ታማኝ መሆንህን፣ ለፍጹም ሰው ፍጹም መሆንህን ታሳያለህ። ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ። አንተ ትሑታንን ታድናለህ፤ ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል። በአንተ ጕልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ፤ በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ። “የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው? ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው። እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ። የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል። ርምጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተሰነካከሉም። “ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤ እስኪጠፉም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም። ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል። ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣ ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከክሃቸው። ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው። ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው። ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አደቀቅኋቸው፤ በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም። “በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ። የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ፤ የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል። ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ። “እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን! አምላኬ የድነቴ ዐለት ከፍ ከፍ ይበል። በቀሌን የሚመልስልኝ፣ አሕዛብንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል። አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ። “ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣ ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል።”
2 ሳሙኤል 22:19-51 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ። ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፥ ወድዶኛልና አዳነኝ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፥ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል፥ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁምና። ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ከሥርዓቱም አልራቅሁምና። በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ። እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ። ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፥ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፥ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ። አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ። አቤቱ፥ አንተ መብራቴ ነህና፥ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል። በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፥ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና። የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው። ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው? ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቃና፥ እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያረታ፥ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው። እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴ የናስ ቀስት እገትራለሁ። የማዳንህንም ጋሻ ሰጠኸኝ፥ ተግሣጽህም አሳደገኝ። አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ፥ አጠፋቸውማለሁ፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። ጮኹ፥ የሚረዳቸውም አልነበረም፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ አልሰማቸውምም። እንደ ምድር ትቢያ ፈጨኋቸው፥ እንደ አደባባይም ጭቃ ረገጥኋቸው፥ ደቀደቅኋቸውም። ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል። የባዕድ ልጆች ደለሉኝ፥ በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ። የባዕድ ልጆች እየጠፉ ይሄዳሉ፥ ከተዘጉ ስፍሮች እየተንቀጠቁ ይወጣሉ። እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ ጠባቂዬም፥ ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴ ጠባቂ አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል፥ በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ፥ አሕዛብን በበታቼ የሚያስገዛ፥ ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፥ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ። አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ። የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው፥ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል።
2 ሳሙኤል 22:19-51 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ። ወደ ሰፊ ቦታ አወጣኝ፤ በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ። እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕናም ይመልስልኛል። እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትያለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም። የእግዚአብሔርን ሕጎች ሁሉ እፈጽማለሁ፤ ሥርዓቱንም ከማክበር ወደ ኋላ አላልኩም። በእርሱ ዘንድ ንጹሕ ነበርኩ፥ ከኃጢአትም ራሴን ጠብቄአለሁ፤ እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና ዋጋዬን ከፈለኝ። አምላክ ሆይ! ለአንተ ታማኞች ለሆኑት ታማኝ ነህ፤ እውነተኞች ለሆኑትም እውነተኛ ነህ። ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፤ ለጠማሞች ግን ተገቢ ዋጋቸውን ትሰጣለህ። ትሑቶችን ታድናለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ታዋርዳለህ። እግዚአብሔር ሆይ! ለእኔ ብርሃኔ ነህ፤ አንተ አምላኬ ጨለማዬን ታበራለህ። በአንተ ርዳታ አንድ የጦር ጓድ አጠቃለሁ፤ አንተ አምላኬም ቅጥሩን ለመዝለል ትረዳኛለህ። የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም ነው፤ ቃሉ የጠራ ነው፤ እርሱን መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ማን ነው አምላክ? ከእርሱስ በቀር መጠጊያ የሚሆን ማነው? ብርታትን የሚሰጠኝና መንገዴን የሚያቃናልኝ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያጠነክራል፤ በከፍታ ቦታዎችም ያለ ሥጋት ለመቆም ያስችለኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ የነሐስን ቀስት መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል። አምላኬ ሆይ! የማዳን ጋሻህ ሰጠኸኝ፤ የአንተ ኀይልም ያጸናኛል። አረማመዴን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም፤ ዳግመኛ እንዳይነሡ አድርጌ እመታቸዋለሁ፤ በእግሬም ሥር ይወድቃሉ። ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ። ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ፤ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ። የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ አደቀቅኋቸው፤ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም እረግጣቸዋለሁ። ከዐመፀኛ ሕዝብ አዳንከኝ፤ በአሕዛብም ላይ ሾምከኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ይገዛልኛል። ባዕዳን ያጐነብሱልኛል፤ ዝናዬን እንደ ሰሙም ይገዙልኛል በፍርሃት ይጨነቃሉ፤ በመንቀጥቀጥም ከምሽጋቸው ወጥተው ወደ እኔ ይመጣሉ። እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል! እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችንም ከበታቼ አድርጎ ያስገዛልኛል። ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ። ጌታ ሆይ! ስለዚህ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ። እርሱ ላነገሠው ንጉሥ ድልን ያጐናጽፈዋል፤ እርሱ ከቀባውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳየዋል፤ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘለዓለም ይህን ያደርጋል።
2 ሳሙኤል 22:19-51 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ ጌታ ግን ደገፈኝ። ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤ ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ። ጌታ እንደጽድቄ መለሰልኝ፤ እንደ እጄም ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ፤ የጌታን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ ከአምላኬ ክፋት በማድረግ አልተለየሁም። ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዓቱም አልራቅሁም። በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤ ራሴንም ከኃጢአት ጠብቄአለሁ። ጌታም እንደጽድቄ፥ በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ። “ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ ሆነህ ትገኛለህ፥ ለቅን ሰው አንተም ቅን ሆነህ ትታያለህ። ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ ሆነህ ትታያለህ፥ ለጠማማ ሰው ግን ጠማማ ሆነህ ትታያለህ። አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤ ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፥ ትዕቢተኞችን ይመለከታል። ጌታ ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤ ጌታም ጨለማዬን ያበራል። በአንተ ርዳታ ሠራዊት አልፌ ወደ ፊት እሮጣለሁ፤ በአምላኬም ኃይል ቅጥሩን እዘላለሁ። የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የጌታም ቃል የጠራ ነው፤ ለሚታመኑበትም ሁሉ ጋሻ ነው፤ ከጌታ በቀር አምላክ ማን ነው፤ ከአምላካችንስ በቀር ዓለት ማን ነው? ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቀና እግዚአብሔር ነው። እግሮቼን እንደ ብሆር እግር ያበረታል፤ በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል። ክንዶቼም የናስ ቀስት መሳብ እንዲችሉ፥ እጆቼን ለጦርነት ያሰለጥናል። የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ምላሽህም ታላቅ አድርጎኛል። እርምጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተሰነካከሉም። ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤ ሳላጠፋቸው ወደ ኋላ አልተመለስሁም። ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ አስጨነቅኻቸው ተመልሰውም እንዳይቆሙ፥ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል። ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። ለርዳታ ጮኹ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ ጌታ ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አደቀቅዃቸው፤ በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም። ከሕዝቤ ጥቃት አዳንከኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ፤ የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤ ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤ እንደ ሰሙኝም በፍጥነት ይታዘዙኛል። ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ። ጌታ ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤ የመዳኔ ዓለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል። የሚበቀልልኝ አምላክ፥ ሕዝቦችን ከሥሬ የሚያስገዛልኝ፤ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ የሚያወጣኝ እርሱ ነው። በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ። ስለዚህ ጌታ ሆይ፥ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም ምስጋና እዘምራለሁ። ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥ የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳያል፥ ይህንንም ለዘለዓለም ያደርጋል።”