1 ነገሥት 17:2-7
1 ነገሥት 17:2-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም እንዲህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ለኤልያስ መጣለት፤ “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ባለው በኮራት ወንዝ ተሸሸግ። ውሃ ከወንዙ ትጠጣለህ፤ ቍራዎችም እዚያው እንዲመግቡህ አዝዣለሁ።” ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘውን ፈጸመ፤ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ኮራት ወንዝ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ። ቍራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር። በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመጣሉ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወንዙ ደረቀ።
1 ነገሥት 17:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ለእርሱ መጣለት “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ በዮርዳኖስም ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸግ። ከወንዙም ትጠጣለህ፤ ቍራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ።” ሄደም፤ እንደ እግዚአብሔር ቃልም አደረገ። ሄዶም በዮርዳኖስ ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተቀመጠ። ቍራዎችም በየጥዋትና በየማታው እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ከወንዙም ይጠጣ ነበር። ከብዙ ቀንም በኋላ በምድር ላይ ዝናብ አልነበረምና ወንዙ ደረቀ።
1 ነገሥት 17:2-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ በዮርዳኖስም ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸግ። ከፈፋው ትጠጣለህ፤ ቁራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ።” ሄደም፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው አደረገ። ሄዶም በዮርዳኖስ ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ተቀመጠ። ቁራዎችም በየጥዋቱና በየማታው እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ከፈፋውም ይጠጣ ነበር። ከብዙ ቀንም በኋላ በምድር ላይ ዝናብ አልነበረምና ፈፋው ደረቀ።
1 ነገሥት 17:2-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም እንዲህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ለኤልያስ መጣለት፤ “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ባለው በኮራት ወንዝ ተሸሸግ። ውሃ ከወንዙ ትጠጣለህ፤ ቍራዎችም እዚያው እንዲመግቡህ አዝዣለሁ።” ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘውን ፈጸመ፤ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ኮራት ወንዝ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ። ቍራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር። በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመጣሉ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወንዙ ደረቀ።
1 ነገሥት 17:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ለእርሱ መጣለት “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ በዮርዳኖስም ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸግ። ከወንዙም ትጠጣለህ፤ ቍራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ።” ሄደም፤ እንደ እግዚአብሔር ቃልም አደረገ። ሄዶም በዮርዳኖስ ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተቀመጠ። ቍራዎችም በየጥዋትና በየማታው እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ከወንዙም ይጠጣ ነበር። ከብዙ ቀንም በኋላ በምድር ላይ ዝናብ አልነበረምና ወንዙ ደረቀ።
1 ነገሥት 17:2-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ፤ “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ እዚያም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ከሪት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሸግ፤ የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቊራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ።” ኤልያስም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሄዶ በከሪት ሸለቆ ተቀመጠ፤ ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቊራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ።
1 ነገሥት 17:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከዚህ በኋላ የጌታ ቃል ወደ ኤልያስ መጣ። “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ እዚያም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ከሪት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሸግ። የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቁራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ።” ኤልያስም ጌታ ባዘዘው መሠረት ሄዶ በከሪት ሸለቆ ተቀመጠ። ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቁራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር። ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ።