መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 17:2-7

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 17:2-7 አማ2000

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤል​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ “ከዚህ ተነ​ሥ​ተህ ወደ ምሥ​ራቅ ሂድ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ትይዩ ባለው በኮ​ራት ፈፋ ውስጥ ተሸ​ሸግ። ከፈ​ፋው ትጠ​ጣ​ለህ፤ ቁራ​ዎ​ችም በዚያ ይመ​ግ​ቡህ ዘንድ አዝ​ዣ​ለሁ።” ሄደም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ። ሄዶም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ትይዩ ባለው በኮ​ራት ፈፋ ተቀ​መጠ። ቁራ​ዎ​ችም በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው እን​ጀ​ራና ሥጋ ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ ከፈ​ፋ​ውም ይጠጣ ነበር። ከብዙ ቀንም በኋላ በም​ድር ላይ ዝናብ አል​ነ​በ​ረ​ምና ፈፋው ደረቀ።