አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 17:2-7

አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 17:2-7 አማ05

ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ፤ “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ እዚያም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ከሪት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሸግ፤ የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቊራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ።” ኤልያስም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሄዶ በከሪት ሸለቆ ተቀመጠ፤ ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቊራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ።