መጽሐፈ ኢዮብ 42:1-5

መጽሐፈ ኢዮብ 42:1-5 አማ54

ኢዮብም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ያለ እውቀት ምክርን የሚሰውር ማን ነው? ስለዚህ እኔ የማላስተውለውን፥ የማላውቀውንም ድንቅ ነገር ተናግሬአለሁ። እባክህ፥ ስማኝ፥ እኔም ልናገር፥ እጠይቅህማለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፥