ኢዮብ 42:1-5

ኢዮብ 42:1-5 NASV

ኢዮብም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤ “አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ። አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው?’ አልኸኝ፤ በርግጥ ያልገባኝን ነገር፣ የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጕዳይ ተናገርሁ። “ ‘ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤ አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ። ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ።