ከዚህ በኋላ ኢዮብ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፦ “አምላክ ሆይ! አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል ዐውቃለሁ፤ የአንተንም ዕቅድ ማሰናከል የሚችል የለም። እኔ የማውቀው በጣም ትንሽ ሆኖ ሳለ ብዙ የምናገረው ለምን እንደ ሆነ ጠይቀሃል። በእርግጥ እኔ ስለማላውቃቸውና እጅግ ድንቅ ስለ ሆነ ነገር ተናግሬአለሁ። ‘አድምጥና ለጥያቄዬ መልስ ስጥ’ ብለኸኛል፤ እኔ እስከ አሁን ስለ አንተ የማውቀው፥ ሰዎች የነገሩኝን በመስማት ብቻ ነበር፤ አሁን ግን በዐይኖቼ አየሁህ።
መጽሐፈ ኢዮብ 42 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢዮብ 42:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች