የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 42

42
ኢዮብ
1ከዚህ በኋላ ኢዮብ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፦
2“አምላክ ሆይ!
አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል ዐውቃለሁ፤
የአንተንም ዕቅድ ማሰናከል የሚችል የለም።
3እኔ የማውቀው በጣም ትንሽ ሆኖ ሳለ
ብዙ የምናገረው ለምን እንደ ሆነ ጠይቀሃል።
በእርግጥ እኔ ስለማላውቃቸውና
እጅግ ድንቅ ስለ ሆነ ነገር ተናግሬአለሁ። #ኢዮብ 38፥2።
4‘አድምጥና ለጥያቄዬ መልስ ስጥ’ ብለኸኛል፤ #38፥3።
5እኔ እስከ አሁን ስለ አንተ የማውቀው፥
ሰዎች የነገሩኝን በመስማት ብቻ ነበር፤
አሁን ግን በዐይኖቼ አየሁህ።
6ከዚህም የተነሣ የተናገርኩት ነገር ስላሳፈረኝ በዐመድና በትቢያ ላይ
ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”
መደምደሚያ
7እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር እነዚህን ነገሮች ከተነጋገረ በኋላ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ስለ እኔ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ትክክለኛውን ነገር ስላልተናገራችሁ እኔ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ ላይ ተቈጥቼአለሁ። 8ስለዚህ አሁን ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እዚያም ስለ ራሳችሁ ኃጢአት የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን ሰምቼ በበደላችሁ መጠን አልቀጣችሁም፤ እናንተ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ትክክል የሆነውን ነገር አልተናገራችሁም።”
9ከዚህ በኋላ ቴማናዊው ኤሊፋዝ፥ ሹሐዊውም ቢልዳድና ናዕማታዊውም ጾፋር ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም የኢዮብን ጸሎት ሰማ።
10ኢዮብ ለሦስቱ ወዳጆቹ ከጸለየ በኋላ እግዚአብሔር እንደገና እንዲበለጽግ አደረገው፤ ዱሮ ከነበረውም ይበልጥ እጥፍ አድርጎ ሰጠው። #ኢዮብ 1፥1-3። 11በዚህ ጊዜ የኢዮብ ወንድሞች፥ እኅቶችና ቀድሞ የሚያውቁት ሰዎች ሁሉ ሊጐበኙት መጡ፤ በቤቱም ከእርሱ ጋር ተመገቡ፥ ሐዘናቸውን በመግለጥ እግዚአብሔር ስላደረሰበት ብርቱ መከራ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም የብርና የወርቅ ቀለበት ስጦታ አደረጉለት።
12እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት። 13እንዲሁም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆችን እንደገና ወለደ። 14ከሴቶች ልጆቹ የመጀመሪያዋን ይሚማ፥ ሁለተኛዋን ቀጺዐ ሦስተኛዋን ቄሬንሀፉክ ብሎ ሰየማቸው። 15በዓለም ላይ የኢዮብን ሴቶች ልጆች በቊንጅና የሚወዳደሩአቸው ሴቶች አልነበሩም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት አካፈላቸው።
16ከዚህም በኋላ ኢዮብ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ ለማየት በቃ። 17ብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ አርጅቶ ሞተ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ