ኦሪት ዘዳግም 32:1-43

ኦሪት ዘዳግም 32:1-43 አማ54

ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ 2 ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ። ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትፈስሳለች፥ 2 ነገሬ እንደ ጠል ትንጠባጠባለች፤ 2 በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ 2 በሣርም ላይ እንደ ካፊያ። የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁና፤ 2 ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ። እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ 2 መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ 2 የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ 2 እርሱ እውነተኛና ቅን ነው። እነርሱ ረከሱ፤ ልጆቹም አይደሉም፤ 2 ነውርም አለባቸው፤ ጠማማና ገልበጥባጣ ትውልድ ናቸው። ደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ 2 ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? 2 የገዛህ አባትህ አይደለምን? 2 የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው። የዱሮውን ዘመን አስብ፥ 2 የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ 2 አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ 2 ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። 2 ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ 2 የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ 2 እንደ እስራኤል ልጆች ቁጥር 2 የአሕዛብን ድንበር አቆመ። የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ 2 ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው። በምድረ በዳ በጥማት፥ 2 የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ 2 ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ 2 እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው። ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ 2 በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ 2 ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ 2 በክንፎቹም አዘላቸው። እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ 2 ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የእርሻውን ፍሬ በላ፤ 2 ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ 2 ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አጠባው፤ የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ 2 ከጠቦት ስብ ጋር፥ 2 የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ 2 ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ 2 ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ። ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ 2 ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ 2 የፈጠረውንም እግዚአብሔርን ተወ፤ 2 የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ። በሌሎች አማልክት አስቀኑት፥ 2 በርኩሰታቸውም አስቈጡት። እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት፥ 2 ለማያውቍቸውም አማልክት፥ 2 በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች 2 አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ። የወለደህን አምላክ ተውህ፥ 2 ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቈጡት 2 እግዚአብሔር አይቶ ጣላቸው። እርሱም አለ፦ ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፤ 2 ፍጻሜያቸው ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ 2 ጠማማ ትውልድ፥ 2 ያልታመኑም ልጆች ናቸው። አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ ቍ 15 በዕብራይስጥ ይሹሩን የሚለውን ግዕዙ ያዕቆብ ይለዋል። 2 በምናምንቴዎቻቸውም አስቈጡኝ፤ 2 እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ 2 በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና፥ 2 እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ 2 ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥ 2 የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች። መከራን እጨምርባቸዋለሁ፤ 2 በፍላጾቼም እወጋቸዋለሁ። በራብ በንዳድ ይጠፋሉ፤ 2 በንዳድና በመራራ ጥፋት ያልቃሉ፤ 2 የአራዊትን ጥርስ፥ 2 የምድርንም እባብ መርዝ እሰድድባቸዋለሁ። ጉልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ 2 በሜዳ ሰይፍ፥ በቤትም ውስጥ ድንጋጤ ያጠፋቸዋል። እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ 2 ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ። ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ 2 እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ 2 እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም 2 እንዳይሉ፥ 2 ስለ ጠላቱ ቁጣ ፈራሁ። ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ 2 ማስተዋልም የላቸውም። አእምሮ ቢኖራቸው፥ 2 ይህንን ያስተውሉ ነበር፥ 2 ፍጻሜያቸውንም ያስቡ ነበር። እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ 2 እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ 2 አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? 2 ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር? አምላካችን እንደ አማልክቶቻቸው አይደለም፤ 2 ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው። ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ 2 ከገሞራም እርሻ ነው፤ 2 ፍሬያቸው ሐሞት ነው፤ 2 ዘለላውም መራራ ነው። የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥ 2 የእፉኝትም ሥራይ ነው። ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ የለምን? 2 በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ 2 የሚመጣባቸውም ነገር ይፈጥናልና 2 እግራቸው ሲሰናከል 2 በቀልና ፍርድ የእኔ ነው። ኃይላቸውም እንደ ደከመ፥ 2 የተዘጋ የተለቀቀም እንደሌለ ባየ ጊዜ 2 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ 2 ስለ ባሪያዎቹም ያዝናል። እርሱም ይላል፦ አማልክቶቻቸው የት ናቸው? 2 ይታመኑባቸው የነበሩት አማልክት? የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ 2 የመጠጥ ቁርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ? 2 እነርሱ ይነሡ፥ ይርዱአችሁም፥ 2 መጠጊያም ይሁኑላችሁ። አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ 2 ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ 2 እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ 2 እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ 2 ከእጄም የሚያድን የለም። እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥ 2 እንዲህም እላለሁ፦ ለዘላለም እኔ ሕያው ነኝና የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ፥ 2 እጄም ፍርድን ትይዛለች፥ 2 ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ 2 ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ። ከተወጉት ከተማረኩትም ደም፥ 2 ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፤ 2 ከጠላት አለቆችም ራስ 2 ሰይፌ ሥጋ ይበላል። የባሪያዎቹን ደም ይበቀላልና፥ 2 ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ 2 ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና 2 እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።