ዘዳግም 32:1-43
ዘዳግም 32:1-43 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሰማያት ሆይ፤ አድምጡ፤ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፤ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ። ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ። እኔ የእግዚአብሔርን ስም ዐውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት አወድሱ! እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው። በርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው። አንተ ሞኝና ጥበብ የጐደለህ ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር የምትመልስለት በዚህ መንገድ ነውን? አባትህ ፈጣሪህ፣ የሠራህና ያበጀህ እርሱ አይደለምን? የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤ አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል። ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣ በእስራኤል ልጆች ቍጥር ልክ፣ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤ የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና። እርሱን በምድረ በዳ፣ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አገኘው፤ ጋሻ ሆነው፤ ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው። ንስር ጐጆዋን በትና፣ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣ እግዚአብሔር ብቻ መራው፤ ምንም ባዕድ አምላክ ዐብሮት አልነበረም። በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የዕርሻንም ፍሬ መገበው። ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው። የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ። ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ። በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስጸያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቈጡት። አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፦ ላላወቋቸው አማልክት፣ ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፣ አባቶቻችሁ ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ። አባት የሆነህን ዐለት ከዳኸው፤ የወለደህን አምላክ ረሳኸው። እግዚአብሔር ይህን አይቶ ናቃቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ ተቈጥቷልና። እርሱም፣ “ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ” አለ፤ ጠማማ ትውልድ፣ የማይታመኑም ልጆች ናቸውና። አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸው አስቈጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በሞኝ ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ። በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል። “በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ። የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድድባቸዋለሁ፤ የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድድባቸዋለሁ። ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ ቤታቸውም ውስጥ ድንጋጤ ይነግሣል፤ ጕልማሳውና ልጃገረዷ፣ ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ። እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ አልሁ፤ ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፣ ‘ድል ያደረገችው እጃችን እንጂ፣ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም’ እንዳይሉ፣ የጠላትን መነሣሣት ሠጋሁ።” አእምሮ የጐደላቸው፣ ማስተዋልም የሌላቸው ሕዝብ ናቸው። አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡ፣ መጨረሻቸውም ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነበር። መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው፣ እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፣ አንድ ሰው እንዴት ሺሑን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺሑን እንዲሸሹ ያደርጋሉ? የእነርሱ መጠጊያ ዐለት እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን አይክዱም። ወይናቸው ከሰዶም ወይን፣ ከገሞራም ዕርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፣ ዘለላቸውም በምሬት የተሞላ ነው። ወይናቸው የእባብ መርዝ፣ የመራዥ እባብም መርዝ ነው። “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧል፤ የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።” ኀይላቸው መድከሙን፣ ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል። እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣ እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ? የመሥዋዕታቸውን ሥብ የበሉ፣ የመጠጥ ቍርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስኪ ይነሡና ይርዷችሁ! እስኪ መጠለያ ይስጧችሁ! “እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም። እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆንሁ እናገራለሁ፤ የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ስዬ፣ እጄ ለፍርድ ስትይዘው፣ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ የሚጠሉኝንም እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ። ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፣ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች፣ የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው።” አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ያነጻልና።
ዘዳግም 32:1-43 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንዲህም አለ፦ “ሰማይ ሆይ፥ አድምጥ፥ ልንገርህ፤ ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ። ትምህርቴንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድርገው፤ ነገሬ እንደ ጠል ይውረድ፤ በእርሻም ላይ እንደ ዝናም፥ በሣርም ላይ እንደ ጤዛ። የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁና፤ ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ። እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው። እነርሱ በደሉ፤ ልጆቹም አይደሉም፤ ነውርም አለባቸው፤ ጠማማና ገልበጥባጣ ትውልድ ናቸው። ደንቆሮ፥ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህን ትመልሳለህን? የፈጠረህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው። የዱሮውን ዘመን አስብ፤ የልጅ ልጅንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ይነግርህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፤ ይተርኩልህማል። ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ የአዳምንም ልጆች በለያቸው ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ አሕዛብን በየድንበራቸው አቆማቸው። ሕዝቡ ያዕቆብም የእግዚአብሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤ እስራኤልም የርስቱ ገመድ ነው። በምድረ በዳ አጠገባቸው፤ በጥማትና በድካም ቦታ፥ በውድማ ከበባቸው፤ መገባቸው፤ መራቸውም፤ እንደ ዐይን ብሌንም ጠበቃቸው። ንስር ጫጩቶቹን በክንፎቹ በታች እንደሚሰበስብ፥ በጎኑም እንደሚያቅፍ፥ በክንፎቹ አዘላቸው፤ በደረቱም ተሸከማቸው። እግዚአብሔር ብቻውን መራቸው፤ ከእነርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። በምድር ኀይል ላይ አወጣቸው፤ የእርሻውንም ፍሬ መገባቸው፤ ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አሳደጋቸው፤ በላሙ ቅቤ፥ በበጉም ወተት፥ ከፍየል ጠቦትና ከላም፥ ከጊደሮችና ከበጎች ስብ ጋር፥ ከፍትግ ስንዴ ጋር መገባቸው፤ የዘለላውንም ደም የወይን ጠጅ አድርገው ጠጡ። ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ። በዚህ በልዩ ጣዖት አነሣሡኝ፤ በርኵሰታቸውም አስመረሩኝ። ለእግዚአብሔር ያይደለ ለአጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ ድንገት ለተገኙ ለማይሠሩና ለማይጠቅሙ አማልክት፥ አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው አማልክት ሠዉ። የወለደህን እግዚአብሔርን ተውህ፤ ያሳደገህን እግዚአብሔርንም ረሳኸው። እግዚአብሔርም አይቶ ቀና፤ በወንዶችና ሴቶች ልጆችም ፈጽሞ ተቈጣ። እርሱም አለ፦ ፊቴን ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ በመጨረሻው ዘመን ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፥ እምነት የሌላቸው ልጆች ናቸውና። አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በጣዖቶቻቸውም አስቈጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ። እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች። ለመከራ እሰበስባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎችንም እጨርስባቸዋለሁ። በራብ ያልቃሉ፤ ለሰማይ ወፎችም መብል ይሆናሉ፤ ኀይላቸውም ይደክማል፥ ከምድር ይጠፉ ዘንድ የምድር አራዊትን ጥርስ፥ ከመርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ። ጐልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ በሜዳ ሰይፍ፥ በቤትም ውስጥ ድንጋጤ ያጠፋቸዋል። እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ። ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ። ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፤ ምግባርና ሃይማኖት የላቸውም። ይህንም ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፤ በሚመጣውም ዘመን አያውቁትም። አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና። አምላካችን እንደ አምላኮቻቸው አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው። ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ ሐረጋቸውም ከገሞራ ነው፤ ፍሬአቸውም ሐሞት ነው፤ ዘለላቸውም መራራ ነው። የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥ የሚገድልም የእፉኝት መርዝ ነው። በእኔ ዘንድ ያለው ትእዛዝ ይህ አይደለምን? በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ስለ አገልጋዮቹም ይራራል፤ በያሉበት መሳለቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይላቸውም እንደ ደከመ፥ በጠላትም እጅ እንደ ወደቁ አይቶአልና። እግዚአብሔርም አለ፦ ትታመኑባቸው የነበሩት አማልክት የት አሉ? የመሥዋዕታቸውን ስብ የምትበሉላቸው፥ የመጠጥ ቍርባናችውንም ወይን የምትጠጡላቸው፥ እነርሱ ይነሡ፤ ይርዱአችሁም፤ የሚያድኑአችሁም ይሁኑላችሁ። እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም። እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥ በቀኜ እምላለሁ፦ ለዘለዓለምም እኔ ሕያው ነኝ እላለሁ። ሰይፌን እንደ መብረቅ እስላታለሁ፤ እጄም ፍርድን ትይዛለች፤ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ። ከተወጉት፥ ከተማረኩትም ደም፥ ፍላጻዎቼን በደም አሰክራለሁ፤ ከጠላት አለቆችም ራስ ሰይፌ ሥጋን ትበላለች። ሰማያት ሁሉ በአንድነት ደስ ይላቸዋል፤ የእግዚአብሔርም መላእክት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ከሕዝቡ ጋር ደስ ይላቸዋል። የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ እርሱ ጽኑዕ ነው ይላሉ፤ የልጆቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ለሚጠላቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋልና፥ እግዚአብሔርም የሕዝቡን ምድር ያነጻል።”
ዘዳግም 32:1-43 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሰማያት ሆይ፤ አድምጡ፤ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፤ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ። ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ። እኔ የእግዚአብሔርን ስም ዐውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት አወድሱ! እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው። በርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው። አንተ ሞኝና ጥበብ የጐደለህ ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር የምትመልስለት በዚህ መንገድ ነውን? አባትህ ፈጣሪህ፣ የሠራህና ያበጀህ እርሱ አይደለምን? የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤ አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል። ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣ በእስራኤል ልጆች ቍጥር ልክ፣ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤ የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና። እርሱን በምድረ በዳ፣ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አገኘው፤ ጋሻ ሆነው፤ ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው። ንስር ጐጆዋን በትና፣ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣ እግዚአብሔር ብቻ መራው፤ ምንም ባዕድ አምላክ ዐብሮት አልነበረም። በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የዕርሻንም ፍሬ መገበው። ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው። የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ። ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ። በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስጸያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቈጡት። አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፦ ላላወቋቸው አማልክት፣ ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፣ አባቶቻችሁ ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ። አባት የሆነህን ዐለት ከዳኸው፤ የወለደህን አምላክ ረሳኸው። እግዚአብሔር ይህን አይቶ ናቃቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ ተቈጥቷልና። እርሱም፣ “ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ” አለ፤ ጠማማ ትውልድ፣ የማይታመኑም ልጆች ናቸውና። አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸው አስቈጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በሞኝ ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ። በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል። “በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ። የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድድባቸዋለሁ፤ የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድድባቸዋለሁ። ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ ቤታቸውም ውስጥ ድንጋጤ ይነግሣል፤ ጕልማሳውና ልጃገረዷ፣ ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ። እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ አልሁ፤ ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፣ ‘ድል ያደረገችው እጃችን እንጂ፣ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም’ እንዳይሉ፣ የጠላትን መነሣሣት ሠጋሁ።” አእምሮ የጐደላቸው፣ ማስተዋልም የሌላቸው ሕዝብ ናቸው። አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡ፣ መጨረሻቸውም ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነበር። መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው፣ እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፣ አንድ ሰው እንዴት ሺሑን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺሑን እንዲሸሹ ያደርጋሉ? የእነርሱ መጠጊያ ዐለት እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን አይክዱም። ወይናቸው ከሰዶም ወይን፣ ከገሞራም ዕርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፣ ዘለላቸውም በምሬት የተሞላ ነው። ወይናቸው የእባብ መርዝ፣ የመራዥ እባብም መርዝ ነው። “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧል፤ የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።” ኀይላቸው መድከሙን፣ ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል። እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣ እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ? የመሥዋዕታቸውን ሥብ የበሉ፣ የመጠጥ ቍርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስኪ ይነሡና ይርዷችሁ! እስኪ መጠለያ ይስጧችሁ! “እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም። እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆንሁ እናገራለሁ፤ የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ስዬ፣ እጄ ለፍርድ ስትይዘው፣ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ የሚጠሉኝንም እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ። ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፣ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች፣ የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው።” አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ያነጻልና።
ዘዳግም 32:1-43 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ 2 ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ። ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትፈስሳለች፥ 2 ነገሬ እንደ ጠል ትንጠባጠባለች፤ 2 በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ 2 በሣርም ላይ እንደ ካፊያ። የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁና፤ 2 ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ። እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ 2 መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ 2 የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ 2 እርሱ እውነተኛና ቅን ነው። እነርሱ ረከሱ፤ ልጆቹም አይደሉም፤ 2 ነውርም አለባቸው፤ ጠማማና ገልበጥባጣ ትውልድ ናቸው። ደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ 2 ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? 2 የገዛህ አባትህ አይደለምን? 2 የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው። የዱሮውን ዘመን አስብ፥ 2 የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ 2 አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ 2 ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። 2 ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ 2 የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ 2 እንደ እስራኤል ልጆች ቁጥር 2 የአሕዛብን ድንበር አቆመ። የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ 2 ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው። በምድረ በዳ በጥማት፥ 2 የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ 2 ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ 2 እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው። ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ 2 በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ 2 ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ 2 በክንፎቹም አዘላቸው። እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ 2 ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የእርሻውን ፍሬ በላ፤ 2 ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ 2 ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አጠባው፤ የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ 2 ከጠቦት ስብ ጋር፥ 2 የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ 2 ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ 2 ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ። ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ 2 ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ 2 የፈጠረውንም እግዚአብሔርን ተወ፤ 2 የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ። በሌሎች አማልክት አስቀኑት፥ 2 በርኩሰታቸውም አስቈጡት። እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት፥ 2 ለማያውቍቸውም አማልክት፥ 2 በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች 2 አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ። የወለደህን አምላክ ተውህ፥ 2 ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቈጡት 2 እግዚአብሔር አይቶ ጣላቸው። እርሱም አለ፦ ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፤ 2 ፍጻሜያቸው ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ 2 ጠማማ ትውልድ፥ 2 ያልታመኑም ልጆች ናቸው። አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ ቍ 15 በዕብራይስጥ ይሹሩን የሚለውን ግዕዙ ያዕቆብ ይለዋል። 2 በምናምንቴዎቻቸውም አስቈጡኝ፤ 2 እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ 2 በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና፥ 2 እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ 2 ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥ 2 የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች። መከራን እጨምርባቸዋለሁ፤ 2 በፍላጾቼም እወጋቸዋለሁ። በራብ በንዳድ ይጠፋሉ፤ 2 በንዳድና በመራራ ጥፋት ያልቃሉ፤ 2 የአራዊትን ጥርስ፥ 2 የምድርንም እባብ መርዝ እሰድድባቸዋለሁ። ጉልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ 2 በሜዳ ሰይፍ፥ በቤትም ውስጥ ድንጋጤ ያጠፋቸዋል። እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ 2 ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ። ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ 2 እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ 2 እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም 2 እንዳይሉ፥ 2 ስለ ጠላቱ ቁጣ ፈራሁ። ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ 2 ማስተዋልም የላቸውም። አእምሮ ቢኖራቸው፥ 2 ይህንን ያስተውሉ ነበር፥ 2 ፍጻሜያቸውንም ያስቡ ነበር። እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ 2 እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ 2 አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? 2 ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር? አምላካችን እንደ አማልክቶቻቸው አይደለም፤ 2 ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው። ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ 2 ከገሞራም እርሻ ነው፤ 2 ፍሬያቸው ሐሞት ነው፤ 2 ዘለላውም መራራ ነው። የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥ 2 የእፉኝትም ሥራይ ነው። ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ የለምን? 2 በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ 2 የሚመጣባቸውም ነገር ይፈጥናልና 2 እግራቸው ሲሰናከል 2 በቀልና ፍርድ የእኔ ነው። ኃይላቸውም እንደ ደከመ፥ 2 የተዘጋ የተለቀቀም እንደሌለ ባየ ጊዜ 2 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ 2 ስለ ባሪያዎቹም ያዝናል። እርሱም ይላል፦ አማልክቶቻቸው የት ናቸው? 2 ይታመኑባቸው የነበሩት አማልክት? የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ 2 የመጠጥ ቁርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ? 2 እነርሱ ይነሡ፥ ይርዱአችሁም፥ 2 መጠጊያም ይሁኑላችሁ። አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ 2 ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ 2 እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ 2 እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ 2 ከእጄም የሚያድን የለም። እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥ 2 እንዲህም እላለሁ፦ ለዘላለም እኔ ሕያው ነኝና የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ፥ 2 እጄም ፍርድን ትይዛለች፥ 2 ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ 2 ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ። ከተወጉት ከተማረኩትም ደም፥ 2 ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፤ 2 ከጠላት አለቆችም ራስ 2 ሰይፌ ሥጋ ይበላል። የባሪያዎቹን ደም ይበቀላልና፥ 2 ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ 2 ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና 2 እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።
ዘዳግም 32:1-43 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሰማይ ሆይ፥ የምናገረውን አድምጥ፤ ምድርም ከአፌ የሚወጣውን ቃል ትስማ፤ ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ የእግዚአብሔርን ስም ዐውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት ተናገሩ። “እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው። በእርሱ ፊት የረከሰ ጠባያቸውን አሳዩ፤ በዚህም የእርሱ ልጆች አለመሆናቸው ይታወቃል፤ እነርሱ የተበላሹና ጠማማ ትውልድ ናቸው። እናንተ ሞኞችና ኅሊና ቢሶች፥ የእግዚአብሔርን ዋጋ የምትከፍሉ በዚህ ዐይነት ነውን? እርሱ የፈጠራችሁ አባታችሁ አይደለምን? የመሠረታችሁስ እርሱ አይደለምን? “የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውን አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ እርሱም ይነግርሃል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ እነርሱም ይተርኩልሃል። ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው። እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው። “በነፋሻማ ባዶ በረሓ በምድረ በዳ አገኘው፤ መከታ ሆነለት፤ ጠበቀውም፤ እንደ ዐይን ብሌኑም ተንከባከበው። በጫጩቶችዋ ላይ እንደምታንዣብብ፥ ጎጆዋን እንደምትጠብቅ ንስር፥ እርሱን ለመያዝ ክንፎቹን ይዘረጋል፤ በክንፎቹም ጫፍ ይደግፈዋል። እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም። “በከፍተኛ ቦታ ላይ አኖረው፤ የምድሩንም ምርት መገበው፤ ከቋጥኝ የተገኘውን ማርና ከድንጋያማ መሬት ከበቀለው ወይራ የተገኘውን ዘይት መገበው። ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ። “እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም። በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤ የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤ መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ። እግዚአብሔርን በጣዖት አምልኮ አስቀኑት፤ በሚያደርጉትም ክፉ ነገር ሁሉ አስቈጡት። ከዚህ በፊት ላላወቁአቸው፥ በቅርቡ አዲስ ለመጡ፥ ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት የቀድሞ አባቶቻቸው ላላመለኩአቸው አማልክት መሥዋዕት አቀረቡ። ያስገኛቸውን አምላክ ተዉ፤ የፈጠራቸውንም እግዚአብሔር ረሱ። “ሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው ስላስቈጡት እግዚአብሔር አስወገዳቸው። ‘ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አያለሁ፤ እነርሱ የተበላሸ ትውልድ እምነት የሚጣልባቸው ልጆች አይደሉም’ አለ። እውነተኛ ባልሆኑ አማልክት አስቀንተውኛል፤ ዋጋቢስ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አስቈጥተውኛል፤ በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል። “ተከታታይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ። የሚጨርስ ራብ በእነርሱ ላይ እልካለሁ፤ በወረርሽኝና በመቅሠፍት ያልቃሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችንና መርዘኛ ተናዳፊ እባቦችን እሰድባቸዋለሁ። በየመንገዱ ላይ ጦርነት ልጅ አልባ ያደርጋቸዋል፤ በቤት ውስጥ ፍርሀት ይሰፍናል፤ ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃናትና ሽማግሌዎችም ያልቃሉ። እኔ ፈጽሜ እደመስሳቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ ነገር ግን ጠላቶቻቸው ‘አሸናፊዎች እኛ ነን እንጂ እግዚአብሔር አይደለም’ ብለው በመታበይ ያስቈጡኛል ብዬ አስባለሁ። “የእስራኤል ሕዝብ አእምሮ ቢሶች ናቸው፤ አያስተውሉምም። ምነው ብልኆች ሆነው ይህን ባስተዋሉና፤ መጨረሻውንም በተገነዘቡ ነበር! ፈጣሪአቸው አሳልፎ ካልሰጣቸውና አምላካቸውም ካልተዋቸው በቀር እንዴት አንዱ ሺሁን ያሳድዳል? ወይም ሁለቱ ዐሥር ሺሁን ያባርራሉ? ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት የእነርሱ አምላክ እንደ እኛ አምላክ አይደለም። ጠላቶቻችን እንደ ሰዶምና ገሞራ የረከሱ ናቸው፤ እነርሱም መራራና መርዘኛ ፍሬ እንደሚሰጥ የወይን ተክል ናቸው። ወይናቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ እንደ ክፉ እፉኝትም መርዝ ነው። “ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል። የምበቀል እኔ ነኝ ለሁሉም እንደየሥራቸው እከፍላለሁ፤ የጥፋታቸው ቀን ስለ ደረሰ ይሰናከላሉ፤ ፈጥነውም ይጠፋሉ። ኀይል ማጣታቸውን ሲያይ፥ እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ ይራራል፤ ነጻም፥ ባሪያም ሳይለይ ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል። እግዚአብሔርም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ጠየቀ፦ ‘የሚተማመኑባቸው አማልክቶቻቸው የት አሉ? ከዚያም የተማመኑበት አለት አማልክቶቻቸውስ የት አሉ’ ይላል። የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ የወይን ቊርባናቸውን የጠጡ አማልክታቸው ተነሥተው ይርዱአቸው፤ መጠጊያም ይሁኑአቸው። “አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም እጄን ወደ ሰማይ ዘርግቼ እንዲህ በማለት እምላለሁ፦ ‘እኔ ለዘለዓለም ሕያው ነኝ፤ የሚያንጸባርቅ ሰይፌን እስለዋለሁ፤ እኔም ፍርድን እፈርዳለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፤ ለሚጠሉኝም ዋጋቸውን እሰጣለሁ። ከተገደሉትና ከተማረኩት ከጠላት መሪዎችም ራስ ደም ፍላጻዎቼን አሰክራለሁ፤ ሰይፌ የጠላትን ሥጋ ይቈራርጣል።’ “ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤ የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።”
ዘዳግም 32:1-43 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ። ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬ እንደ ጠል ይንጠባጠብ፤ በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ በሣርም ላይ እንደ ካፊያ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ዝናብ፥ የጌታን ስም አውጃለሁ፤ ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ!” “እርሱ ዐለት፥ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፥ የታመነ አምላክ፥ ተንኮል የሌለበት፥ እርሱ ቀጥተኛና ጻድቅ ነው። በእርሱ ፊት ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው። አንተ የማታስተውልና ኀሊና ቢስ ሕዝብ፥ ለጌታ ምላሽህ እንዲህ ነው? እርሱ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና የሠራህ ያጸናህም እርሱ አይደለምን?” “የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፥ አባትህን ጠይቅ፥ እርሱም ያስታውቅሃል፥ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ እነርሱም ይነግሩሃል። ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ የሰውን ልጆች በለየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቍጥር የአሕዛብን ድንበር አቆመ። ሕዝቡ የጌታ ድርሻ ነው፥ ያዕቆብም የተለየ ርስቱ ነው።” “በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት በምድረ በዳ አገኘው፥ መከታ ሆነለት፥ ተጠነቀቀለትም፥ እንደ ዐይን ብሌኑም ጠበቀው። ንስር ጎጆዋን ቆስቁሳ፥ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ይወስደዋል፥ በክንፎቹም ያዝለዋል። ጌታ ብቻውን መራው፥ ከእርሱም ጋር ባዕድ አምላክ አልነበረም።” “በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፥ የምድሩንም ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ ማር፥ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው። የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።” “ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፥ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፥ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፥ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ። በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፥ በርኩሰታቸውም አስቆጡት። አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ። የወለደህን አምላክ ተውህ፥ የፈጠረህን እግዚአብሔር ረሳህ።” “ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቆጡት ጌታ አይቶ ጣላቸው። እርሱም እንዲህ አለ፦ ‘ጠማማ ትውልድ፥ ያልታመኑም ልጆች ናቸውና፥ ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፥ ፍጻሜያቸው ምን እንደሆነ አያለሁ። አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በምናምንቴዎቻቸውም አስቆጡኝ፥ እኔም በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፥ በማያስተውል ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ። እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’” “‘በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ፤ ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ። በሚያቃጥል ንዳድና በራብ ያልቃሉ፤ በወረርሽኝ መቅሠፍት ይጠፋሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችን፥ ከሚሳቡ መርዘኛ እባቦችን ጋር እሰድባቸዋለሁ። ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ በየመንገዱ ላይ በጦርነት፥ በቤትም ውስጥ በድንጋጤ ያጠፋቸዋል። ፈጽሜ እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፤’ አልኩ። ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ ‘እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ ጌታ ይህን ሁሉ አላደረገም’ እንዳይሉ፥ ስለ ጠላት ትንኮሳ አሰብኩ።” “ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው። አስተዋዮች ቢሆኑ፥ ይህንን በተገነዘቡ፥ ፍጻሜያቸውንም ባሰቡ ነበር! እርሱ አንባቸው ካልሸጣቸው፥ ጌታም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ እንዴት አንዱ ሺህን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺህ ያባርራሉ? ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም። ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤ ፍሬያቸው በመርዝ የተሞላ፥ ዘለላቸውም መራራ ነው። ወይናቸው የእባብ መርዝ፥ የጨካኝ እፉኝት መርዝ ነው።” “ይህስ በእኔ ዘንድ የተጠበቀ፥ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? በቀልና ብድራት መመለስ የእኔ ነው፤ እግራቸው የሚሰናከልበት ጊዜው፥ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧልና፥ የሚመጣባቸው ፍርድ ይፈጥናል። ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ለአገልጋዮቹም ያዝናል። ኃይላቸውም እንደደከመ፥ የታሰረም ሆነ የተለቀቀ እንደሌለ ሲያዩ፥ እርሱም ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ ‘ይታመኑባቸው የነበሩት አምባዎች፥ አማልክቶቻቸው የት ናቸው? እነዚያ የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ የመጠጥ መለማመኛቸውንም ወይን የጠጡ? እስቲ እነርሱ ይነሡና ይርዱአችሁ! እስቲ መጠጊያም ይሁኑላችሁ!’” “እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ እገድላለሁ፤ በሕይወትም አኖራለሁ፤ እኔ አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም። እጄን ወደ ሰማይ ዘርግቼ፥ ለዘለዓለም እኔ ሕያው እንደሆንኩ፥ እምላለሁ። የሚያንጸባርቅ ሰይፌን ከሳልኩ፥ እጄም ለፍርድ ካነሳችው፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እመልሳለሁ። ከተገደሉት ደም፥ ከተማረኩትም ደም፥ ከጠላት አለቆችም ራስ፥ ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፥ ሰይፌም ሥጋ ይቆራርጣል።” “የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”