መዝ​ሙረ ዳዊት 84:5-8

መዝ​ሙረ ዳዊት 84:5-8 አማ2000

ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ቈ​ጣን፥ ቍጣ​ህ​ንም ለልጅ ልጅ አታ​ስ​ረ​ዝም። አንተ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተመ​ለ​ስ​ልን፥ አድ​ነ​ንም፤ ሕዝ​ብ​ህም በአ​ንተ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን አሳ​የን፥ አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ስጠን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝን አደ​ም​ጣ​ለሁ፤ ሰላ​ምን ለሕ​ዝ​ቡና ለጻ​ድ​ቃኑ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ እርሱ ለሚ​መ​ልሱ ይና​ገ​ራ​ልና።