መዝሙር 84:5-8

መዝሙር 84:5-8 NASV

ብፁዓን ናቸው፤ አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ፤ በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣ የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤ የበልጕም ዝናብ ያረሰርሰዋል። ከኀይል ወደ ኀይል ይሸጋገራሉ፤ እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል። የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ አድምጠኝ። ሴላ