መዝሙር 84:5-8
መዝሙር 84:5-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለዘለዓለም አትቈጣን፥ ቍጣህንም ለልጅ ልጅ አታስረዝም። አንተ አምላካችን ሆይ፥ ተመለስልን፥ አድነንም፤ ሕዝብህም በአንተ ደስ ይላቸዋል። አቤቱ፥ ምሕረትህን አሳየን፥ አቤቱ፥ ማዳንህን ስጠን። እግዚአብሔር አምላኬ የሚናገረኝን አደምጣለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለጻድቃኑ፥ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።
ያጋሩ
መዝሙር 84 ያንብቡመዝሙር 84:5-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ብፁዓን ናቸው፤ አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ፤ በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣ የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤ የበልጕም ዝናብ ያረሰርሰዋል። ከኀይል ወደ ኀይል ይሸጋገራሉ፤ እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል። የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ አድምጠኝ። ሴላ
ያጋሩ
መዝሙር 84 ያንብቡ