መዝሙረ ዳዊት 84
84
ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1አቤቱ፦ ምድርህን ይቅር አልኽ።#ዕብ. ለምድርህ ሞገስን አደረግህ” ይላል።
የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።
2የሕዝብህን ኀጢአት ይቅር አልህ፤
ዐበሳቸውንም ሁሉ ሰወርህ።
3መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፤
ከቍጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።
4አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ፥ መልሰን፥
ቍጣህንም ከእኛ መልስ።
5ለዘለዓለም አትቈጣን፥
ቍጣህንም ለልጅ ልጅ አታስረዝም።
6አንተ አምላካችን ሆይ፥ ተመለስልን፥ አድነንም፤
ሕዝብህም በአንተ ደስ ይላቸዋል።
7አቤቱ፥ ምሕረትህን አሳየን፥
አቤቱ፥ ማዳንህን ስጠን።
8እግዚአብሔር አምላኬ የሚናገረኝን አደምጣለሁ፤
ሰላምን ለሕዝቡና ለጻድቃኑ፥
ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።
9ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ
ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው።
10ይቅርታና ቅንነት ተገናኙ፤
ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።
11ቅንነት ከምድር በቀለች፥
ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተ።
12እግዚአብሔርም ምሕረቱን ይሰጣል፥
ምድርም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ምድራችን” ይላል። ፍሬዋን ትሰጣለች።
13ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፥
ፍለጋውንም በመንገድ ውስጥ ይተዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 84: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ