የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 85

85
የዳ​ዊት ጸሎት።
1አቤቱ፥ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል ስማ​ኝም፥
ድሃና ምስ​ኪን ነኝና።
2እኔ የዋህ ነኝና ነፍ​ሴን ጠብ​ቃት፤
አም​ላኬ ሆይ፥ አን​ተን የታ​መ​ነ​ውን ባሪ​ያ​ህን አድ​ነው።
3አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለ​ሁና ይቅር በለኝ።
4የባ​ሪ​ያ​ህን ነፍስ ደስ አሰ​ኛት፥
ነፍ​ሴን ወደ አንተ አነ​ሣ​ለ​ሁና።
5አቤቱ፥ አንተ መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነህና፥
ይቅ​ር​ታ​ህም#ዕብ. “ምሕ​ረ​ትህ” ይላል። ለሚ​ጠ​ሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።
6አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ምጥ፥
የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ስማ።
7ትሰ​ማ​ኛ​ለ​ህና በመ​ከ​ራዬ ቀን ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ።
8አቤቱ፥ ከአ​ማ​ል​ክት የሚ​መ​ስ​ልህ የለም፥
እንደ ሥራ​ህም ያለ የለም።
9የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ይምጡ፥
አቤቱ፥ በፊ​ት​ህም ይስ​ገዱ፥
ስም​ህ​ንም ያክ​ብሩ፤
10አቤቱ፥ ድን​ቅን የም​ታ​ደ​ርግ አንተ ታላቅ ነህና፥
አን​ተም ብቻ​ህን ታላቅ አም​ላክ ነህና፥
11አቤቱ መን​ገ​ድ​ህን ምራኝ፥
በእ​ው​ነ​ት​ህም እሄ​ዳ​ለሁ፤
ስም​ህ​ንም ለመ​ፍ​ራት ልቤን ደስ ይለ​ዋል።
12አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስም​ህን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤
13ምሕ​ረ​ትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥
ነፍ​ሴ​ንም ከታ​ች​ኛ​ዪቱ ሲኦል አድ​ነ​ሃ​ታ​ልና።
14አም​ላኬ ሆይ፥ ዐመ​ፅ​ኞች በእኔ ላይ ተነ​ሥ​ተ​ዋል፥
የክ​ፉ​ዎ​ችም ማኅ​በር ነፍ​ሴን ፈለ​ጉ​አት፤
አን​ተ​ንም በፊ​ታ​ቸው አላ​ደ​ረ​ጉ​ህም።
15አቤቱ፥ አንተ መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነህ፤
መዓ​ትህ የራቀ፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ እው​ነ​ተ​ኛም ነህ።
16ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፥ ይቅር በለ​ኝም፤
ለባ​ሪ​ያህ ኀይ​ልን ስጠው፥ የሴት ባሪ​ያ​ህ​ንም ልጅ አድን።
17ምል​ክ​ት​ንም ለመ​ል​ካም ከእኛ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከእኔ ጋር” ይላል። ጋር አድ​ርግ፤
ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጠላ​ቶ​ችም” ይላል። ይዩ፥ ይፈ​ሩም፥
አቤቱ፥ አንተ ረድ​ተ​ኸ​ና​ልና፥#ዕብ. እና ግሪክ. ሰባ. ሊ. “ረድ​ተ​ኸ​ኛ​ልና ደስም አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ኛ​ልና” ይላል። ደስም አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ና​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ