የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 83

83
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በዋ​ሽ​ንት የቆሬ ልጆች መዝ​ሙር።
1የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥
ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ እጅግ የተ​ወ​ደዱ ናቸው።
2አቤቱ፥ ነፍሴ አደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህን በመ​ው​ደድ ደስ አላት፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ትና​ፍ​ቃ​ለች” ይላል።
ልቤም ሥጋ​ዬም በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አላ​ቸው።
3ወፍ ለእ​ር​ስዋ ቤትን አገ​ኘች፥
ዋኖ​ስም ጫጩ​ቶ​ች​ዋን የም​ታ​ኖ​ር​በት ቤት አገ​ኘች፤
የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ንጉ​ሤም አም​ላ​ኬም ሆይ፥
እርሱ መሠ​ዊ​ያህ ነው።
4በቤ​ትህ የሚ​ኖሩ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው፤
ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያመ​ስ​ግ​ኑ​ሃል።
5አቤቱ፥ ርዳ​ታው ከአ​ንተ ዘንድ የሆ​ነ​ለት፥
በል​ቡም የላ​ይ​ኛ​ውን መን​ገድ የሚ​ያ​ስብ ሰው ብፁዕ ነው።
6በል​ቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወ​ሰ​ን​ኻ​ቸው ስፍራ
የሕግ መም​ህር በረ​ከ​ትን ይሰ​ጣ​ልና።#ከዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል።
7ከኀ​ይል ወደ ኀይ​ልም ይሄ​ዳል፥#ዕብ. “ይሄ​ዳሉ” ይላል።
የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ በጽ​ዮን ይታ​ያል።#ዕብ. “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት” ይላል።
8የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማኝ፤
የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ሆይ፥ አድ​ም​ጠኝ።
9አቤቱ፥ መታ​መ​ኔን እይ​ልኝ፥
ወደ ቀባ​ኸ​ውም ፊት ተመ​ል​ከት።
10ከአ​እ​ላፍ ይልቅ በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ችህ አን​ዲት ቀን ትሻ​ላ​ለች፤
በኃ​ጥ​ኣን ድን​ኳ​ኖች ከመ​ቀ​መጥ ይልቅ፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እጣል ዘንድ መረ​ጥሁ።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ምጽ​ዋ​ት​ንና#ዕብ. “ፀሐ​ይና ጋሻ ነውና” ይላል። እው​ነ​ትን ይወ​ድ​ዳ​ልና፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርና ሞገ​ስን ይሰ​ጣል፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ን​ነት የሚ​ሄ​ዱ​ትን
ከበ​ረ​ከቱ አያ​ሳ​ጣ​ቸ​ውም።
12አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥
በአ​ንተ የታ​መነ ሰው ብፁዕ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ