መጽሐፈ መዝሙር 84:5-8

መጽሐፈ መዝሙር 84:5-8 አማ05

ወደ ጽዮን ተራራ መንፈሳዊ ጒዞ ለማድረግ የሚፈልጉና የአንተን ርዳታ የሚያገኙ እንዴት የተባረኩ ናቸው? ባካ በተባለው ደረቅ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ እግዚአብሔር ምንጭን ያፈልቅላቸዋል፤ የበልግም ዝናብ ኩሬዎችን ይሞላቸዋል። በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤ የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል። የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ! አድምጠኝ።