ወደሚኖሩበትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ የቀና መንገድን መራቸው። የእግዚአብሔርን ምሕረት ለሰው ልጆችም ያደረገውን ድንቁን ንገሩ፤ የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና። በጨለማና በሞትም ጥላ የተቀመጡ፥ በችግር በብረትም የታሰሩ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ አማረሩ፥ የልዑልንም ምክር ስለ አስቈጡ፥ ልባቸው በመከራ ደከመ፤ ታመሙ የሚረዳቸውንም አጡ። በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው። ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣቸው፥ እግር ብረታቸውንም ሰበረ። የእግዚአብሔርን ምሕረት ለሰው ልጆችም ያደረገውን ድንቁን ንገሩ፤ የናሱን ደጆች ሰብሮአልና፥ የብረቱንም መወርወሪያ ቀጥቅጦአልና። ከበደላቸው ጎዳና ተቀበላቸው፥ በኀጢአታቸው ተሠቃይተዋልና። ሰውነታቸውም መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ። በተጨነቁም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው። ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው። የእግዚአብሔርን ምሕረት ለሰው ልጆችም ያደረገውን ድንቁን ንገሩ፤
መዝሙረ ዳዊት 106 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 106:7-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos