የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 106:7-21

መዝሙር 106:7-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ፣ ታምራትህን አላስተዋሉም፤ የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤ በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ። እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ ስለ ስሙ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው። ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልተረፈም። ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤ በዝማሬም አመሰገኑት። ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም። በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው። በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ። ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች። እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ። በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ። በግብጽ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤

መዝሙር 106:7-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ ምድር እርሱ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ አላስተዋሉም፤ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስታወሱም፤ በቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁ። ሆኖም ኀያል ሥልጣኑን ለማሳወቅ ስለ ክብሩ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን በገሠጸው ጊዜ ደረቀ፤ ጥልቁን ውሃ እንደ በረሓ አድርጎ ሕዝቦቹን እየመራ አሻገራቸው። ከሚጠሉአቸውም ሰዎች እጅ አዳናቸው፤ ከጠላቶቻቸውም እጅ ታደጋቸው። ጠላቶቻቸውን ግን ውሃው አሰጠማቸው፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት የቀረ አልነበረም። ከዚህ በኋላ በተስፋ ቃሉ አመኑ፤ የምስጋናም መዝሙር ዘመሩለት። ይሁን እንጂ ያደረገላቸውን ድንቅ ነገር ሁሉ ወዲያውኑ ረሱ፤ የእርሱንም ምክር ሳይጠብቁ የራሳቸውን ፈቃድ አደረጉ። በበረሓ ሳሉ ብዙ ነገር ተመኙ፤ እግዚአብሔርንም ተፈታተኑት። እርሱ የለመኑትን ሁሉ ሰጣቸው፤ ነገር ግን የሚያመነምን በሽታ አመጣባቸው። በበረሓ ሰፍረው ሳሉ በሙሴና የእግዚአብሔር ቅዱስ አገልጋይ በሆነው በአሮን ቀኑባቸው። ምድርም ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ አቤሮንንና ቤተሰቡንም ከደነቻቸው። በተከታዮቻቸውም ላይ እሳት ወረደ፤ እነዚያንም ክፉ ሰዎች አቃጠለ። በኮሬብ ሳሉ የወርቅ ጥጃ ሠሩ፤ ለዚያም ጣዖት ሰገዱ። የእግዚአብሔርንም ክብር ሣር በሚበላ እንስሳ ምስል ለወጡ። በግብጽ ሳሉ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ።

መዝሙር 106:7-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ የቀና መን​ገ​ድን መራ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤ የተ​ራ​በ​ችን ነፍስ አጥ​ግ​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ች​ንም ነፍስ በበ​ረ​ከት ሞል​ቶ​አ​ልና። በጨ​ለ​ማና በሞ​ትም ጥላ የተ​ቀ​መጡ፥ በች​ግር በብ​ረ​ትም የታ​ሰሩ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ አማ​ረሩ፥ የል​ዑ​ል​ንም ምክር ስለ አስ​ቈጡ፥ ልባ​ቸው በመ​ከራ ደከመ፤ ታመሙ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ው​ንም አጡ። በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው። ከጨ​ለ​ማና ከሞት ጥላ አወ​ጣ​ቸው፥ እግር ብረ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤ የና​ሱን ደጆች ሰብ​ሮ​አ​ልና፥ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ ቀጥ​ቅ​ጦ​አ​ልና። ከበ​ደ​ላ​ቸው ጎዳና ተቀ​በ​ላ​ቸው፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ተሠ​ቃ​ይ​ተ​ዋ​ልና። ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም መብ​ልን ሁሉ ተጸ​የ​ፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ። በተ​ጨ​ነ​ቁም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው። ቃሉን ልኮ ፈወ​ሳ​ቸው፥ ከጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤

መዝሙር 106:7-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ፣ ታምራትህን አላስተዋሉም፤ የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤ በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ። እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ ስለ ስሙ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው። ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልተረፈም። ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤ በዝማሬም አመሰገኑት። ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም። በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው። በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ። ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች። እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ። በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ። በግብጽ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤

መዝሙር 106:7-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ ምድር እርሱ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ አላስተዋሉም፤ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስታወሱም፤ በቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁ። ሆኖም ኀያል ሥልጣኑን ለማሳወቅ ስለ ክብሩ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን በገሠጸው ጊዜ ደረቀ፤ ጥልቁን ውሃ እንደ በረሓ አድርጎ ሕዝቦቹን እየመራ አሻገራቸው። ከሚጠሉአቸውም ሰዎች እጅ አዳናቸው፤ ከጠላቶቻቸውም እጅ ታደጋቸው። ጠላቶቻቸውን ግን ውሃው አሰጠማቸው፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት የቀረ አልነበረም። ከዚህ በኋላ በተስፋ ቃሉ አመኑ፤ የምስጋናም መዝሙር ዘመሩለት። ይሁን እንጂ ያደረገላቸውን ድንቅ ነገር ሁሉ ወዲያውኑ ረሱ፤ የእርሱንም ምክር ሳይጠብቁ የራሳቸውን ፈቃድ አደረጉ። በበረሓ ሳሉ ብዙ ነገር ተመኙ፤ እግዚአብሔርንም ተፈታተኑት። እርሱ የለመኑትን ሁሉ ሰጣቸው፤ ነገር ግን የሚያመነምን በሽታ አመጣባቸው። በበረሓ ሰፍረው ሳሉ በሙሴና የእግዚአብሔር ቅዱስ አገልጋይ በሆነው በአሮን ቀኑባቸው። ምድርም ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ አቤሮንንና ቤተሰቡንም ከደነቻቸው። በተከታዮቻቸውም ላይ እሳት ወረደ፤ እነዚያንም ክፉ ሰዎች አቃጠለ። በኮሬብ ሳሉ የወርቅ ጥጃ ሠሩ፤ ለዚያም ጣዖት ሰገዱ። የእግዚአብሔርንም ክብር ሣር በሚበላ እንስሳ ምስል ለወጡ። በግብጽ ሳሉ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ።

መዝሙር 106:7-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥ የፍቅርህንም ብዛት አላሰቡም፥ በቀይ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ። ስለ ስሙ፥ ኃይሉንም ለማስታወቅ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን ገሠጸው፥ እርሱም ደረቀ፥ እንደ ምድረ በዳ በጥልቁ መራቸው። ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው። ያሳደዱአቸውንም ውኃ ዋጣቸው፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም። በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ። ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ ምክሩን እንኳን አልጠበቁም። በምድረ በዳም በምኞትን ተቃጠሉ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። የለመኑትንም ሰጣቸው፥ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ። ሙሴንም፥ ጌታ የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው። ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፥ በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባም ክፉዎችን አቃጠላቸው። በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ። ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገርንም በቀይ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።