የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 106:7-22

መዝሙረ ዳዊት 106:7-22 መቅካእኤ

አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥ የፍቅርህንም ብዛት አላሰቡም፥ በቀይ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ። ስለ ስሙ፥ ኃይሉንም ለማስታወቅ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን ገሠጸው፥ እርሱም ደረቀ፥ እንደ ምድረ በዳ በጥልቁ መራቸው። ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው። ያሳደዱአቸውንም ውኃ ዋጣቸው፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም። በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ። ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ ምክሩን እንኳን አልጠበቁም። በምድረ በዳም በምኞትን ተቃጠሉ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። የለመኑትንም ሰጣቸው፥ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ። ሙሴንም፥ ጌታ የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው። ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፥ በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባም ክፉዎችን አቃጠላቸው። በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ። ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገርንም በቀይ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።