የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 106:7-21

መዝሙር 106:7-21 NASV

አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ፣ ታምራትህን አላስተዋሉም፤ የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤ በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ። እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ ስለ ስሙ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው። ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልተረፈም። ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤ በዝማሬም አመሰገኑት። ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም። በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው። በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ። ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች። እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ። በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ። በግብጽ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤