የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 106:7-21

መጽሐፈ መዝሙር 106:7-21 አማ05

የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ ምድር እርሱ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ አላስተዋሉም፤ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስታወሱም፤ በቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁ። ሆኖም ኀያል ሥልጣኑን ለማሳወቅ ስለ ክብሩ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን በገሠጸው ጊዜ ደረቀ፤ ጥልቁን ውሃ እንደ በረሓ አድርጎ ሕዝቦቹን እየመራ አሻገራቸው። ከሚጠሉአቸውም ሰዎች እጅ አዳናቸው፤ ከጠላቶቻቸውም እጅ ታደጋቸው። ጠላቶቻቸውን ግን ውሃው አሰጠማቸው፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት የቀረ አልነበረም። ከዚህ በኋላ በተስፋ ቃሉ አመኑ፤ የምስጋናም መዝሙር ዘመሩለት። ይሁን እንጂ ያደረገላቸውን ድንቅ ነገር ሁሉ ወዲያውኑ ረሱ፤ የእርሱንም ምክር ሳይጠብቁ የራሳቸውን ፈቃድ አደረጉ። በበረሓ ሳሉ ብዙ ነገር ተመኙ፤ እግዚአብሔርንም ተፈታተኑት። እርሱ የለመኑትን ሁሉ ሰጣቸው፤ ነገር ግን የሚያመነምን በሽታ አመጣባቸው። በበረሓ ሰፍረው ሳሉ በሙሴና የእግዚአብሔር ቅዱስ አገልጋይ በሆነው በአሮን ቀኑባቸው። ምድርም ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ አቤሮንንና ቤተሰቡንም ከደነቻቸው። በተከታዮቻቸውም ላይ እሳት ወረደ፤ እነዚያንም ክፉ ሰዎች አቃጠለ። በኮሬብ ሳሉ የወርቅ ጥጃ ሠሩ፤ ለዚያም ጣዖት ሰገዱ። የእግዚአብሔርንም ክብር ሣር በሚበላ እንስሳ ምስል ለወጡ። በግብጽ ሳሉ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ።