የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 103

103
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ነፍሴ ሆይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባርኪ” ይላል።
አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤
መታ​መ​ን​ንና የጌ​ት​ነ​ትን ክብር ለበ​ስህ።
2ብር​ሃ​ንን እንደ ልብስ ተጐ​ና​ጸ​ፍህ፤
ሰማ​ይ​ንም እንደ መጋ​ረጃ ዘረ​ጋህ፤
3እል​ፍ​ኙን በውኃ የሚ​ሠራ፥
ደመ​ናን መሄ​ጃው የሚ​ያ​ደ​ርግ፥
በነ​ፋስ ክን​ፍም የሚ​ሄድ፥
4መላ​እ​ክ​ቱን መን​ፈስ፥
አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም የእ​ሳት ነበ​ል​ባል የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው።
5ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ፥
ምድ​ርን መሠ​ረ​ታት፥ አጸ​ና​ትም።
6ጥል​ቁም እንደ ልብስ ክዳኗ ነው፥
በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ውኆች ይቆ​ማሉ።
7ከተ​ግ​ሣ​ጽ​ህም የተ​ነሣ ይሸ​ሻሉ፥
ከነ​ጐ​ድ​ጓ​ድ​ህም ድምፅ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤
8ወደ ተራ​ሮች ይወ​ጣሉ፥
ወደ ሜዳ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ህ​ላ​ቸው ስፍ​ራም ይወ​ር​ዳሉ፥
9እን​ዳ​ያ​ል​ፉ​ትም ድን​በር አደ​ረ​ግ​ህ​ላ​ቸው፥
ምድ​ርን ይከ​ድኑ ዘንድ እን​ዳ​ይ​መ​ለሱ።
10ምን​ጮ​ችን ወደ ቆላ​ዎች የሚ​ልክ፤
በተ​ራ​ሮች መካ​ከል ውኆች ያል​ፋሉ፤
11የዱር አራ​ዊ​ትን ሁሉ ያጠ​ጣሉ፥
የበ​ረሃ አህ​ዮ​ችም ጥማ​ታ​ቸ​ውን ያረ​ካሉ።
12የሰ​ማይ ወፎ​ችም በዚያ ይኖ​ራሉ፤
በዋ​ሻው መካ​ከ​ልም ይጮ​ኻሉ።
13ተራ​ሮ​ችን ከው​ስ​ጣ​ቸው የሚ​ያ​ጠ​ጣ​ቸው፤
ከሥ​ራህ ፍሬ ምድር ትጠ​ግ​ባ​ለች።
14እህ​ልን ከም​ድር ያወጣ ዘንድ፥
ለም​ለ​ሙን ለሰው ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት፥
ሣር​ንም ለእ​ን​ስሳ ያበ​ቅ​ላል።
15ወይን የሰ​ውን ልብ ደስ ያሰ​ኛል፥
ዘይ​ትም ፊትን ለማ​ብ​ራት ነው።
እህ​ልም የሰ​ውን ኀይል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ልብ” ይላል። ያጠ​ነ​ክ​ራል።
16የዱር ዛፎች ሁሉ፥
የተ​ከ​ል​ኸው የሊ​ባ​ኖስ ዝግ​ባም ይጠ​ግ​ባሉ።
17በዚ​ያም ዎፎች ይዋ​ለ​ዳሉ፥
የሸ​መላ ቤትም ይጐ​ራ​በ​ታ​ቸ​ዋል።
18ረጃ​ጅም ተራ​ራ​ዎች ለዋ​ሊ​ያ​ዎች፥
ድን​ጋ​ዮ​ችም ለአ​ሽ​ኮ​ኮ​ዎች መሸሻ ናቸው።
19ጨረ​ቃን በጊ​ዜው ፈጠ​ርህ፤
ፀሐ​ይም መግ​ቢ​ያ​ውን ያው​ቃል።
20ጨለ​ማን ታመ​ጣ​ለህ ሌሊ​ትም ይሆ​ናል፤
በእ​ር​ሱም የዱር አራ​ዊት ሁሉ ይወ​ጡ​በ​ታል።
21የአ​ን​በ​ሶች ግል​ገ​ሎች ያገ​ሣሉ፥ ይነ​ጥ​ቃ​ሉም፥
ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይሻሉ።
22ፀሐይ ስት​ወጣ ይገ​ባሉ፥
በየ​ዋ​ሻ​ቸ​ውም ይው​ላሉ።
23ሰው ወደ ተግ​ባሩ ይሰ​ማ​ራል፥
እስ​ኪ​መ​ሽም ድረስ ሲሠራ ይው​ላል።
24አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ታላቅ ነው፤
ሁሉን በጥ​በብ አደ​ረ​ግህ፥
የፈ​ጠ​ር​ኸ​ውም ፍጥ​ረት ምድ​ርን ሞላ።
25ይህች ባሕር ታላ​ቅና ሰፊ ናት፤
በዚያ ስፍር ቍጥር የሌ​ለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ፥
ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች እን​ስ​ሶች አሉ።
26በዚያ ላይ መር​ከ​ቦች ይሄ​ዳሉ፥
በዚ​ያም ላይ የፈ​ጠ​ር​ኸው ዘንዶ ይጫ​ወ​ታል።
27ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ
እነ​ዚህ ሁሉ አን​ተን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ።
28በሰ​ጠ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤
እጅ​ህን ፈት​ተህ ከቸ​ር​ነ​ትህ የተ​ነሣ ሁሉን ታጠ​ግ​ባ​ለህ።
29ፊት​ህን ብት​መ​ልስ ግን ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤
ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ታወ​ጣ​ለህ፥ ይሞ​ታ​ሉም፥
ወደ አፈ​ራ​ቸ​ውም ይመ​ለ​ሳሉ።
30መን​ፈ​ስ​ህን ትል​ካ​ለህ፥ ይፈ​ጠ​ራ​ሉም፥
የም​ድ​ር​ንም ፊት ታድ​ሳ​ለህ።
31የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሁን፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው ደስ ይለ​ዋል።
32ምድ​ርን ያያል፥ እን​ድ​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥም ያደ​ር​ጋል፤
ተራ​ሮ​ችን ይዳ​ስ​ሳል፥ ይጤ​ሳ​ሉም።
33በሕ​ይ​ወቴ ሳለሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ፥
ለአ​ም​ላ​ኬም በም​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ እዘ​ም​ራ​ለሁ።
34በቃ​ሌም ደስ አሰ​ኘ​ዋ​ለሁ፥#ዕብ. “ቃሌ ለእ​ርሱ ይጣ​ፍጥ” ይላል።
እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ኛል።
35ኃጥ​ኣን ከም​ድር ይጠ​ፋሉ፥
ዐመ​ፀ​ኞ​ችም እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ሩም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይጥፉ ... አይ​ኑር” ይላል።
ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ነፍሴ ሆይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኝ” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ