የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 101

101
ባዘ​ነና ልመ​ና​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባፈ​ሰሰ ጊዜ የባ​ሕ​ታዊ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የድሃ” ይላል። ጸሎት።
1አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማኝ፥
ጩኸ​ቴም ወደ ፊትህ ይድ​ረስ።
2በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤
ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤
በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።
3ዘመኔ እንደ ጢስ አል​ቋ​ልና፥
አጥ​ን​ቶቼም እንደ ሣር ደር​ቀ​ዋ​ልና።
4ተቀ​ሠ​ፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ።
እህል መብ​ላት ተረ​ስ​ቶ​ኛ​ልና
5ከጩ​ኸቴ ድምፅ የተ​ነሣ ሥጋዬ በአ​ጥ​ን​ቶቼ ላይ ተጣ​በቀ።#ዕብ. እና ግሪክ “አጥ​ን​ቶቼ ከሥ​ጋየ ጋር ተጣ​በቁ” ይላል።
6እንደ ሜዳ አህያ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እር​ኩም” ይላል። ሆንኹ፤
ሌሊት በወና ቤት እን​ዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ።
7ተጋሁ፥ በሰ​ገ​ነ​ትም እን​ደ​ሚ​ኖር ብቸኛ ድን​ቢጥ ሆንሁ።
8ጠላ​ቶቼ ሁል​ጊዜ ይሰ​ድ​ቡ​ኛል፥
የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም ተማ​ማ​ሉ​ብኝ።
9አመ​ድን እንደ እህል ቅሜ​አ​ለ​ሁና፥
መጠ​ጤ​ንም ከእ​ን​ባዬ ጋር ጠጥ​ቻ​ለ​ሁና፥
10ከቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍት የተ​ነሣ፥
አን​ስ​ተኽ ጥለ​ኸ​ኛ​ልና።
11ዘመ​ኔም እንደ ጥላ አለፈ፤
እኔም እንደ ሣር ደር​ቄ​አ​ለሁ።
12አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለህ፥
መታ​ሰ​ቢ​ያ​ህም ለልጅ ልጅ ነው።
13አንተ ተነሥ፥ ጽዮ​ን​ንም ይቅር በላት፥
ይቅር ትላት ዘንድ ጊዜዋ ነውና፥ ዘመ​ን​ዋም ደር​ሶ​አ​ልና፤
14ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ድን​ጋ​ዮ​ች​ዋን ወድ​ደ​ዋ​ልና፥
መሬ​ቷ​ንም አክ​ብ​ረ​ው​ታ​ልና።
15አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ስም​ህን፥
ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ ክብ​ር​ህን ይፍሩ፤
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን ይሠ​ራ​ታ​ልና፥
በክ​ብ​ሩም ይገ​ለ​ጣ​ልና።
17ወደ ድሆች ጸሎት ተመ​ለ​ከተ፥
ልመ​ና​ቸ​ው​ንም አል​ና​ቀም፥
18ይህ​ችም ለሚ​መጣ ትው​ልድ ተጻ​ፈች፥#ዕብ. “ይህ ለሚ​መ​ጣው ትው​ልድ ይጻፍ” ይላል።
የሚ​ፈ​ጠ​ርም ሕዝብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤
19ከሰ​ማይ ሆኖ መቅ​ደ​ሱን ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ ምድ​ርን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤
20የእ​ስ​ረ​ኞ​ችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥
የተ​ገ​ደ​ሉ​ት​ንም ሰዎች ልጆች ያድን ዘንድ፤
21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በጽ​ዮን
ምስ​ጋ​ና​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይነ​ግሩ ዘንድ፤
22አሕ​ዛብ በአ​ን​ድ​ነት በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ
ነገ​ሥ​ታ​ትም#መን​ግ​ሥ​ታ​ትም። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገዙ ዘንድ።
23በኀ​ይሉ ጎዳና መለ​ሳ​ቸው፥
የዘ​መ​ኔን ማነስ ንገ​ረኝ።
24በዘ​መኔ አኩ​ሌታ አት​ው​ሰ​ደኝ፤
ዓመ​ቶ​ችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።
25አቤቱ፥ አንተ አስ​ቀ​ድ​መህ ምድ​ርን መሠ​ረ​ትህ፥
ሰማ​ያ​ትም የእ​ጅህ ሥራ ናቸው።
26እነ​ርሱ ይጠ​ፋሉ፥ አንተ ግን ትኖ​ራ​ለህ፥
ሁሉ እንደ ልብስ ያረ​ጃል፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. በብዙ ቍጥር።
እንደ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ትለ​ው​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ ይለ​ወ​ጡ​ማል፤
27አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥
ዓመ​ት​ህም ከቶ አያ​ል​ቅም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. በብዙ ቍጥር።
28የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም ልጆች ይኖ​ራሉ፥
ዘራ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ናል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ