የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 100

100
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።
2እዘ​ም​ራ​ለሁ፥ ንጹሕ መን​ገ​ድ​ንም አስ​ተ​ው​ላ​ለሁ፤
ወደ እኔ መቼ ትመ​ጣ​ለህ?
በቤቴ መካ​ከል በልቤ ቅን​ነት እሄ​ዳ​ለሁ።
3በዐ​ይኔ ፊት ክፉ ነገ​ርን አላ​ኖ​ር​ሁም፤
ዐመፃ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ጠላሁ።
4ጠማማ ልብም አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ኝም፤
ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላ​ወ​ቅ​ሁም።
5ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ውር የሚ​ያ​ማን እር​ሱን አሳ​ደ​ድሁ፤
በዐ​ይኑ ትዕ​ቢ​ተኛ የሆ​ነ​ውና ልቡ የሚ​ሳ​ሳው ከእኔ ጋር አይ​ተ​ባ​በ​ርም።
6ከእኔ ጋር አኖ​ራ​ቸው ዘንድ
ዐይ​ኖቼ ወደ ምድር ምእ​መ​ናን ናቸው፤
በን​ጹሕ መን​ገድ የሚ​ሄድ እርሱ ያገ​ለ​ግ​ለ​ኛል።
7ትዕ​ቢ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ በቤቴ መካ​ከል አይ​ኖ​ርም፥
ዐመ​ፃን የሚ​ና​ገር በፊቴ አይ​ጸ​ናም።
8ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ፥
የም​ድ​ርን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሁሉ በማ​ለዳ እገ​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ