የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 99

99
የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1በም​ድር ሁሉ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፥
2በደ​ስ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ፥
በሐ​ሤ​ትም ወደ ፊቱ ግቡ።
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ሆነ ዕወቁ፤
እርሱ ፈጠ​ረን፥ እኛም አይ​ደ​ለ​ንም፤
እኛስ ሕዝቡ የመ​ሰ​ማ​ር​ያ​ውም በጎች ነን።
4ወደ ደጆቹ በመ​ገ​ዛት፥
ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ቹም በም​ስ​ጋና ግቡ፤
አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም አክ​ብሩ፥
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም፥
እው​ነ​ቱም ለልጅ ልጅ ነውና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ