መዝሙረ ዳዊት 98
98
የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ደነገጡ፤
በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ፥ ምድርን አነዋወጣት።
2እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤
እርሱም በአሕዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
3ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመሰግናል፥
ግሩምና ቅዱስ ነውና።
4ክቡር ንጉሥ ፍርድን ይወድዳል፤
አንተ በኀይልህ ጽድቅን#ዕብ. “ቅንነትን” ይላል። አጸናህ፥
ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።
5ፈጣሪያችን#ዕብ. “አምላካችን” ይላል። እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥
ከእግሩ መረገጫ በታችም ይሰግዱለታል።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከእግሩ መረገጫ በታች ይሰግዱለታል ቅዱስ ነውና” ይላል።
6ሙሴና አሮን በክህነታቸው ቅዱሳን ናቸውና#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሙሴና አሮን በካህናት መካከል” ይላል።
ሳሙኤልም ስሙን ከሚጠሩት ጋራ፤
እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።
7በደመና ዐምድም ተናገራቸው፤
ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።
8አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፤
አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥
በሥራቸው ሁሉ ግን ትበቀላቸዋለህ።
9አምላካችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥
በተቀደሰው ተራራ ይሰግዱለታል፤
አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 98: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ