የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 97

97
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግኑ፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ፥
የቀኙ ማዳን፥ የተ​ቀ​ደሰ ክን​ዱም ድንቅ ነውና።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማዳ​ኑን አሳየ።#ዕብ. “አስ​ታ​ወቀ” ይላል።
በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ቃል ኪዳ​ኑን ገለጠ።
3ለያ​ዕ​ቆብ ይቅ​ር​ታ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት እው​ነ​ቱን አሰበ፤
የም​ድር ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን እዩ።
4በም​ድር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፤
አመ​ስ​ግኑ፥ ደስም ይበ​ላ​ችሁ፥ ዘም​ሩም።
5ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ሰ​ንቆ፥
በመ​ሰ​ን​ቆና በዝ​ማሬ ድምፅ ዘምሩ።
6በነ​ጋ​ሪ​ትና በመ​ለ​ከት ድምፅ፥
በን​ጉሡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እልል በሉ።
7ባሕር በሞ​ላዋ፥
ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይና​ወጡ።
8ወን​ዞ​ችም በአ​ን​ድ​ነት በእጅ ያጨ​ብ​ጭቡ፥
ተራ​ሮች ደስ ይበ​ላ​ቸው፥
9ለም​ድር በዚያ ይፈ​ረ​ድ​ላ​ታ​ልና።
ለዓ​ለ​ምም በእ​ው​ነት ይፈ​ረ​ድ​ላ​ታ​ልና።
ለአ​ሕ​ዛ​ብም በቅ​ን​ነት ይፈ​ረ​ዳል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ