መዝሙረ ዳዊት 100
100
የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ምሕረትንና ፍርድን እዘምርልሃለሁ።
2እዘምራለሁ፥ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፤
ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ?
በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ።
3በዐይኔ ፊት ክፉ ነገርን አላኖርሁም፤
ዐመፃ የሚያደርጉትን ጠላሁ።
4ጠማማ ልብም አልተከተለኝም፤
ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅሁም።
5ባልንጀራውን በስውር የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፤
በዐይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም።
6ከእኔ ጋር አኖራቸው ዘንድ
ዐይኖቼ ወደ ምድር ምእመናን ናቸው፤
በንጹሕ መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።
7ትዕቢትን የሚያደርግ በቤቴ መካከል አይኖርም፥
ዐመፃን የሚናገር በፊቴ አይጸናም።
8ዐመፃን የሚያደርጉትን ሁሉ ከእግዚአብሔር ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥
የምድርን ኀጢአተኞች ሁሉ በማለዳ እገድላቸዋለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 100: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ