የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 2

2
1በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ#ዕብ. “በአ​ር​ጤ​ክ​ስስ” ይላል። በሃ​ያ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በኔ​ሳን ወር የወ​ይን ጠጅ በፊቱ#ግሪ​ክ​ኛው “በፊቴ” ይላል። ነበር፤ ጠጁ​ንም አን​ሥቼ ለን​ጉሡ ሰጠ​ሁት። በፊ​ቱም ሌላ ሰው አል​ነ​በ​ረም።#ዕብ. “ቀድሞ ግን ያለ ኀዘን እኖር ነበር” ይላል። 2ንጉ​ሡም፥ “ሳት​ታ​መም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኀዘን ነው እንጂ ሌላ አይ​ደ​ለም” አለኝ። እጅ​ግም ብዙ አድ​ርጌ ፈራሁ። 3ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኑር፤ የአ​ባ​ቶች መቃ​ብር ያለ​ባት ከተማ ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና ፊቴ ስለ ምን አያ​ዝን?” አል​ሁት። 4ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ። 5ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉ​ሡን ደስ ቢያ​ሰ​ኝህ፥ ባሪ​ያ​ህም በፊ​ትህ ሞገስ ቢያ​ገኝ፥ እሠ​ራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባ​ቶች መቃ​ብር ከተማ ስደ​ደኝ” አል​ሁት። 6ንግ​ሥ​ቲ​ቱም፦#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዕቅ​ብት” ይላል። በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጣ ሳለች ንጉሡ፥ “መን​ገ​ድህ እስከ መቼ ድረስ ይሆ​ናል? መቼስ ትመ​ለ​ሳ​ለህ?” አለኝ። ንጉ​ሡም ይሰ​ድ​ደኝ ዘንድ ደስ አለው፤ እኔም ጊዜ​ውን ነገ​ር​ሁት፤ እር​ሱም አሰ​ና​በ​ተኝ። 7ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሥ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ ሀገር እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ሱኝ በወ​ንዝ ማዶ#“በወ​ንዝ ማዶ” የሚ​ባ​ለው የኤ​ፍ​ራ​ጥስ ምዕ​ራ​ባዊ ክፍል ነው። ላሉት ገዦች ደብ​ዳቤ ይስ​ጠኝ፤ 8በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና።
9በወ​ን​ዙም ማዶ ወዳ​ሉት ሀገረ ገዦች መጥቼ የን​ጉ​ሡን ደብ​ዳ​ቤ​ዎች ሰጠ​ኋ​ቸው። ንጉ​ሡም ከእኔ ጋር የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለ​ቆ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ልኮ ነበር። 10ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ። 11ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረ​ስሁ፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥሁ። 12በሌ​ሊ​ትም ተነ​ሣሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ር​ገው ዘንድ በልቤ ያኖ​ረ​ውን ለማ​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ሁም፤ ተቀ​ም​ጬ​በት ከነ​በ​ረው እን​ስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እን​ስሳ አል​ነ​በ​ረም። 13በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለ​ስም ምን​ጭና#ዕብ. “ወደ ዘን​ዶም ምንጭ” ይላል። ወደ ጕድፍ መጣ​ያው በር ሄድሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር፥ በእ​ሳ​ትም የተ​ቃ​ጠ​ሉ​ትን በሮ​ች​ዋን ተመ​ለ​ከ​ትሁ። 14ወደ ምን​ጩም በርና ወደ ንጉ​ሡም መዋኛ አለ​ፍሁ፤ ተቀ​ም​ጬ​በት የነ​በ​ረው እን​ስ​ሳም የሚ​ያ​ል​ፍ​በት ስፍራ አል​ነ​በ​ረም። 15በሌ​ሊ​ትም በፈ​ፋው በኩል ወጥቼ ቅጥ​ሩን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤#ግሪኩ “ቅጥ​ሩን እያ​የሁ አለ​ቀ​ስሁ” ይላል። በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ገባሁ፤ እን​ዲ​ሁም ተመ​ለ​ስሁ። 16ጠባ​ቆች#ዕብ. “ሹሞች” ይላል። ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁም አላ​ወ​ቁም ነበር፤ ለአ​ይ​ሁ​ድና ለካ​ህ​ናቱ፥ ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለሹ​ሞ​ቹም፥ ሥራም ይሠሩ ለነ​በ​ሩት ለሌ​ሎች እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ገና አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም ነበር።
17እኔም፥ “እኛ ያለ​ን​በ​ትን ጕስ​ቍ​ልና፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ፈረ​ሰች፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠሉ ታያ​ላ​ችሁ። አሁ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ መሳ​ለ​ቂያ እን​ዳ​ን​ሆን ኑና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው። 18የአ​ም​ላ​ኬም እጅ በእኔ ላይ መል​ካም እንደ ሆነች፥ ንጉ​ሡም የነ​ገ​ረ​ኝን ቃል ነገ​ር​ኋ​ቸው። “ተነሡ እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው።#ዕብ. “እነ​ር​ሱም እን​ነ​ሣና እን​ሥራ አሉ” ይላል። እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለበጎ ሥራ አበ​ረቱ። 19ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ። 20እኔም መልሼ፥ “የሰ​ማይ አም​ላክ ያከ​ና​ው​ን​ል​ናል፤ እኛም ንጹ​ሓን ባሪ​ያ​ዎቹ ተነ​ሥ​ተን እን​ሠ​ራ​ለን፤ እና​ንተ ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዕድል ፋን​ታና መብት፥ መታ​ሰ​ቢ​ያም የላ​ች​ሁም” አል​ኋ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ