እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው። የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። “ተነሡ እንሥራ” አልኋቸው። እጆቻቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።