መጽሐፈ ኢዮብ 16
16
1ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ፦
2“እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤
እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ።
3የመጣላችሁን ሁሉ ያለ ልክ ትናገራላችሁ፦
ትከራከሩኝ ዘንድስ ምን አስቸገርኋችሁ?
4እኔ ደግሞ እናንተ እንደምትናገሩ እናገር ነበር፤
ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ብትሆን ኖሮ፥
5እኔም ነገርን እነግራችሁ ነበር፤
ራሴንም በእናንተ ላይ እነቀንቅ ነበር።
6ባፌም ኀይል ቢኖረኝ ኖሮ፥
ከንፈሬን ባልገታሁም ነበር፥
የምናገረውንም ባሻሻልሁ ነበር፤
7እኔ ብናገር ቍስሌ አይድንም፤
ዝም ብልም ሕማሜ ይብስብኛል።
8አሁን ግን የዕብድ ቍርጥራጭና ብጥስጣሽ አደረግኸኝ፤
እኔንም መያዝህ ምስክር ሆነችብኝ፤
9ሐሰቴም በእኔ ላይ ተነሣች፤
በፊቴም ተከራከረችብኝ።
10በቍጣው ጣለኝ፤
ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤
ፍላጻዎቹንም በእኔ ላይ ፈተነ።
11ዐይኖችን አፍዝዞ ጋረደኝ፤
በተሳለ ጦርም ጕልበቴን ወግቶ ጣለኝ።
በአንድነትም ከበቡኝ።
12እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፤
በክፉዎችም እጅ ጣለኝ።
13ተዘልዬ ስኖርም ጣለኝ፤ የራስ ጠጕሬን ይዞ ነጨው፤
እንደ ዓላማም አድርጎ አቆመኝ፤
እንደ ጉበኛም ተመለከተኝ።
14በጦር ከበቡኝ፤
ኵላሊቴንም ወጉኝ፤ እነርሱም አልራሩልኝም፤
ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሱ።
15በውድቀት ላይ ውድቀትን አደረሱብኝ፤
ኀያላኑ እየሠገጉ ሮጡብኝ።
16በቍርበቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤
መከራዬ#ዕብ. “ቀንዴ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኀይሌ” ይላል።። በመሬት ላይ በዛች።
17ሆዴ በልቅሶ ተቃጠለ፤
የሞት ጥላን በቅንድቦች ላይ አያለሁ፤
18ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤
ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
19መሬት ሥጋዬን ይሸፍነው ይሆን?
ደሜስ ይፈስስ ይሆን?
የምጮህበትስ ቦታ አላገኝ ይሆን?
20“አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፤
የሚያውቅልኝም በአርያም ነው።
21ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ፥
ዐይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ።
22የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥
ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመሟገት ምነው በቻለ!
23የተቈጠሩ ዘመኖች ደረሱ፤
እኔም ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 16: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ