መጽሐፈ ኢዮብ 17
17
1ነፍሴን የሚያወጣት ያስጨንቀኛል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. ይለያሉ።
መቃብርንም እመኘዋለሁ፤ ግን አላገኘውም፤
2እየለመንሁ ደከምሁ፤#ዕብ. “አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ” ይላል።
ምንስ አደርጋለሁ?
ባዕዳንም ገንዘቤን ሰረቁኝ።
3ከእኔ ጋር አጋና የሚማታ ማን ነው?
4ልባቸውንም ከጥበብ ሰውረኸዋል፤
ስለዚህ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
5ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥
የልጆቹ ዐይኖች ይጨልማሉ።
6ለአሕዛብም ምሳሌ አደረግኸኝ፤
መሳቂያና መዘባበቻም ሆንኋቸው።
7ዐይኖች ከእንባ የተነሣ ፈዘዙ፥
ሁሉም እጅግ ተጸየፉኝ።
8ደስታዬን ተማምኛት ነበር፤ ነገር ግን ጠፋችብኝ፤
አግባብስ ወደ ኃጥኣን ትመለስ ዘንድ ነው።
9ነገር ግን ወደ መንገዴ እንደ ምመለስ እተማመናለሁ፤
እጆችም የነጹ ናቸውና፤ ደስታዬን አገኛታለሁ።
10ነገር ግን እናንተ ሁሉ ወደዚህ መጥታችሁ ታዩኛላችሁ፤
በእናንተ ዘንድ እውነትን አላገኘሁምና።
11“ዘመኖች በጩኸት አለቁ፤
የልቤ ሥርም ተቈረጠ።
12ቀኑ ሌሊት ሆነብኝ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሌሊቱን ወደ ቀን ለወጥሁ” ይላል።
ከጨለማውም የተነሣ ብርሃኑ አጭር ነው።#ግእዙ “ወጽልመት ውስተ ገጸ ብርሃን ገብዐኒ” ይላል።
13ብዘገይም ሲኦል ቤቴ ናት፤
ምንጣፌም በጨለማ ተነጥፎአል።
14ሞትን፦ አንተ አባቴ ነህ አልሁት፤
ትሎችንም እናንተ እናቴም ወንድሞቼም ናችሁ አልኋቸው።
15እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ናት?
ዳግመኛስ መልካም ነገርን አያታለሁን?
16ከእኔስ ጋር ወደ መቃብር ትወርዳለችን?
አብረንስ በመሬት ውስጥ እንቀበራለንን?”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 17: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ