መጽሐፈ ኢዮብ 18
18
የበልዳዶስ ንግግር
1አውኬናዊው#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሱሓዊው” ይላል። በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
2“ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው?
እኛም እንድንነግርህ ታገሥ።
3ስለ ምንስ እንደ እንስሳ በፊትህ ዝም አልን?
4መከራው ይገባሃል፤ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ ምንድን ነው?
ከሰማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን?#ግእዙ “አልቦኑ ዘይኄይስ እምኔከ በታሕተ ሰማይ” ይላል።
ወይስ ተራራዎች ከመሠረታቸው ይናወጣሉን?
5“የኀጢኣተኞች መብራት ይጠፋል፥
ነበልባላቸውም ብልጭ አይልም።
6ብርሃኑ በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፤
መብራቱም በላዩ ይጠፋል።
7የተዋረዱ ሰዎች ንብረቱን ይወስዳሉ፤
ምክሩም ትጥለዋለች።
8እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፤
በመረብም ትታሠራለች፤
9አሽክላዎች በላዩ ይመጣሉ፤
የተጠሙትም በእርሱ ይበረታሉ፤
10በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመዱ ተሰውራለች፤
የሚጐትተውም በመንገዱ ላይ ነው።
11መከራ በዙሪያው ታጠፋዋለች፤
ብዙ ጠላቶችም ከእግሩ በታች ይመጣሉ።
12ኀይሉ በራብ ትደክማለች።
አስጨናቂ መቅሠፍትም ተዘጋጅቶለታል።
13ጭኖቹ ይበሰብሳሉ።
ሞትም መልካም ሕዋሶቹን ይበላል።
14ጤንነት ከሥጋው ትርቃለች።
መከራው ትጸናለች፤
እግዚአብሔርም ይበቀለዋል።
15በሌሊት በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፤
የእርሱም መልካም ነገር በዲን ይበተናል።
16ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፤
ፍሬውም ከላዩ ይረግፋል።
17መታሰቢያውም ከምድር ይጠፋል፤
በምድርም ስም አይቀርለትም።
18ከብርሃን ወደ ጨለማ አርቀው ያፈልሱታል።
19ከሕዝቡ መካከል የሚራራለት የለም፤
ቤቱ ከሰማይ በታች አይቀርለትም።
20ነገር ግን ባዕድ በንብረቱ ላይ ተድላ ያደርጋል፤
ድሃው በእርሱ ያጕረመርማል።
ፊተኞቹም ይደነቃሉ።
21የኀጢኣተኞች ቤት እንዲህ ነው፤
እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 18: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ