መጽሐፈ ኢዮብ 19
19
የኢዮብ መልስ
1ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ፦
2“ነፍሴን የምትነዘንዙአት፥
በቃላችሁስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው?
ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገብኝ ዕወቁ፤
3ዐሥር ጊዜ#“ዐሥር ጊዜ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ትናገሩኛላችሁ፥ ትሰድቡኛላችሁም፤
በሰውነቴ ላይ በጠላትነት ስትነሡብኝ አታፍሩም።
4በእውነት እኔ ከበደልሁ፤
ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች።
የማላውቀውንም ነገር ተናገርሁ፤
ነገሬም ስንፍና ነው እንጂ በየጊዜው አይደለም።
5ወዮልኝ! አፋችሁን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ታደርጋላችሁና፤
ትጓደዱብኛላችሁ፤ ትዘልፉኛላችሁም።
6እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ አወከኝ፥
መዓቱንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ።
7እነሆ፥ በዘለፋ እደክማለሁ፤
አልናገርምም፤ አሰምቼም እጮኻለሁ፤
ነገር ግን ፍርድ የለኝም።
8ዙሪያዬ ታጥሯል፤ መተላለፊያም የለኝም፤
በፊቴም ጨለማን ጋርዶበታል።
9ክብሬን ገፈፈኝ፤
ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወሰደ።
10በዚህና በዚያ አፈረሰኝ፤ እኔም ሄድሁ፤
ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ቈረጠው።
11በታላቅ ቍጣም ያዘኝ
እንደ ጠላትም ቈጠረኝ።
12ሠራዊቱ አብረው በእኔ ላይ መጡ፥
የሚሸምቁብኝም መንገዴን ከበቡ፥
13“ወንድሞች ተለዩኝ፥
ከእኔ ይልቅ ባዕዳንን ወደዱ።
ጓደኞችም አላዘኑልኝም።
14ዘመዶች አልተረዱኝም፥
ስሜንም የሚያውቁ ረሱኝ።
15ቤተሰቦችና ሴቶች አገልጋዮች ሊያዩኝ አልፈቀዱም፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንግዳ ሆንሁባቸው” ይላል።
እንደ መጻተኛም አስመሰሉኝ።
16አገልጋዮችን እጠራቸዋለሁ፤
እነርሱ ግን ቸል ይሉኛል፤
በአፌም እለማመጣቸዋለሁ።
17ሚስቴን እለማመጣታለሁ፤
እርስዋ ግን ትጠቃቀስብኛለች፤
የቤተሰቤንም ልጆች ፈጽሜ አቈላምጣቸዋለሁ።
18ለዘለዓለም ተስፋ ቈረጡብኝ።
ብነሣም በእኔ ላይ ሐሜት ይናገራሉ።
19ያዩኝ ሁሉ ተጸየፉኝ፤
እኔ የምወድዳቸውም በላዬ ተነሡ።
20ቍርበቴ ከሥጋዬ ጋር ይበጣጠሳል።
አጥንቶቼም ይፋጩብኛል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አጥንቶቼ በጥርሶች ተያዙ” ይላል።
21እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤
የእግዚአብሔር እጅ ዳስሳኛለችና።
22ስለ ምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ?
ከሥጋዬስ ስለምን አትጠግቡም?
23ቃሌን ማን በጻፈው!
ማንስ በመጽሐፍ ውስጥ ለዘለዓለም ባተመው!
24ማን በብረት ብርዕና በእርሳስ፥
በዓለት ላይ በቀረፀው!
25እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥
በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥
26ይህ ቍርበቴም ከጠፋ በኋላ፥
በዚያ ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።
27እኔ ራሴ አየዋለሁ፤ ዐይኖቼም ይመለከቱታል፤
ከእኔም ሌላ አይደለም።
ሁሉም በብብቴ ተፈጸመ።
28“በፊቱ ምን እንናገራለን?
የነገሩ ሥርም በእርሱ ዘንድ ተገኝቶአል ብትሉ፥
29እናንተ ሐሣርን ፍሩአት፥
ቍጣ በኃጥኣን ላይ ይመጣልና፤
ያንጊዜም ክፋታቸው ከየት እንደ ሆነ ያውቃሉ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 19: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ