የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 19

19
የኢ​ዮብ መልስ
1ኢዮ​ብም መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“ነፍ​ሴን የም​ት​ነ​ዘ​ን​ዙ​አት፥
በቃ​ላ​ች​ሁስ የም​ታ​ደ​ቅ​ቁኝ እስከ መቼ ነው?
ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ብኝ ዕወቁ፤
3ዐሥር ጊዜ#“ዐሥር ጊዜ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ትና​ገ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ትሰ​ድ​ቡ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤
በሰ​ው​ነቴ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት ስት​ነ​ሡ​ብኝ አታ​ፍ​ሩም።
4በእ​ው​ነት እኔ ከበ​ደ​ልሁ፤
ስሕ​ተቴ ከእኔ ጋር ትኖ​ራ​ለች።
የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ነገር ተና​ገ​ርሁ፤
ነገ​ሬም ስን​ፍና ነው እንጂ በየ​ጊ​ዜው አይ​ደ​ለም።
5ወዮ​ልኝ! አፋ​ች​ሁን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ጋ​ላ​ች​ሁና፤
ትጓ​ደ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ትዘ​ል​ፉ​ኛ​ላ​ች​ሁም።
6እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ከኝ፥
መዓ​ቱ​ንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ።
7እነሆ፥ በዘ​ለፋ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤
አል​ና​ገ​ር​ምም፤ አሰ​ም​ቼም እጮ​ኻ​ለሁ፤
ነገር ግን ፍርድ የለ​ኝም።
8ዙሪ​ያዬ ታጥ​ሯል፤ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያም የለ​ኝም፤
በፊ​ቴም ጨለ​ማን ጋር​ዶ​በ​ታል።
9ክብ​ሬን ገፈ​ፈኝ፤
ዘው​ዴ​ንም ከራሴ ላይ ወሰደ።
10በዚ​ህና በዚያ አፈ​ረ​ሰኝ፤ እኔም ሄድሁ፤
ተስ​ፋ​ዬ​ንም እንደ ዛፍ ቈረ​ጠው።
11በታ​ላቅ ቍጣም ያዘኝ
እንደ ጠላ​ትም ቈጠ​ረኝ።
12ሠራ​ዊቱ አብ​ረው በእኔ ላይ መጡ፥
የሚ​ሸ​ም​ቁ​ብ​ኝም መን​ገ​ዴን ከበቡ፥
13“ወን​ድ​ሞች ተለ​ዩኝ፥
ከእኔ ይልቅ ባዕ​ዳ​ንን ወደዱ።
ጓደ​ኞ​ችም አላ​ዘ​ኑ​ል​ኝም።
14ዘመ​ዶች አል​ተ​ረ​ዱ​ኝም፥
ስሜ​ንም የሚ​ያ​ውቁ ረሱኝ።
15ቤተ​ሰ​ቦ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ሊያ​ዩኝ አል​ፈ​ቀ​ዱም፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እን​ግዳ ሆን​ሁ​ባ​ቸው” ይላል።
እንደ መጻ​ተ​ኛም አስ​መ​ሰ​ሉኝ።
16አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን እጠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤
እነ​ርሱ ግን ቸል ይሉ​ኛል፤
በአ​ፌም እለ​ማ​መ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።
17ሚስ​ቴን እለ​ማ​መ​ጣ​ታ​ለሁ፤
እር​ስዋ ግን ትጠ​ቃ​ቀ​ስ​ብ​ኛ​ለች፤
የቤ​ተ​ሰ​ቤ​ንም ልጆች ፈጽሜ አቈ​ላ​ም​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።
18ለዘ​ለ​ዓ​ለም ተስፋ ቈረ​ጡ​ብኝ።
ብነ​ሣም በእኔ ላይ ሐሜት ይና​ገ​ራሉ።
19ያዩኝ ሁሉ ተጸ​የ​ፉኝ፤
እኔ የም​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ውም በላዬ ተነሡ።
20ቍር​በቴ ከሥ​ጋዬ ጋር ይበ​ጣ​ጠ​ሳል።
አጥ​ን​ቶቼም ይፋ​ጩ​ብ​ኛል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አጥ​ን​ቶቼ በጥ​ር​ሶች ተያዙ” ይላል።
21እና​ንተ ወዳ​ጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ዳስ​ሳ​ኛ​ለ​ችና።
22ስለ ምን እና​ንተ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታሳ​ድ​ዱ​ኛ​ላ​ችሁ?
ከሥ​ጋ​ዬስ ስለ​ምን አት​ጠ​ግ​ቡም?
23ቃሌን ማን በጻ​ፈው!
ማንስ በመ​ጽ​ሐፍ ውስጥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባተ​መው!
24ማን በብ​ረት ብር​ዕና በእ​ር​ሳስ፥
በዓ​ለት ላይ በቀ​ረ​ፀው!
25እኔን ግን የሚ​ቤ​ዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥
በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን በም​ድር ላይ እን​ዲ​ቆም፥
26ይህ ቍር​በ​ቴም ከጠፋ በኋላ፥
በዚያ ጊዜ ከሥ​ጋዬ ተለ​ይቼ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳይ አው​ቃ​ለሁ።
27እኔ ራሴ አየ​ዋ​ለሁ፤ ዐይ​ኖቼም ይመ​ለ​ከ​ቱ​ታል፤
ከእ​ኔም ሌላ አይ​ደ​ለም።
ሁሉም በብ​ብቴ ተፈ​ጸመ።
28“በፊቱ ምን እን​ና​ገ​ራ​ለን?
የነ​ገሩ ሥርም በእ​ርሱ ዘንድ ተገ​ኝ​ቶ​አል ብትሉ፥
29እና​ንተ ሐሣ​ርን ፍሩ​አት፥
ቍጣ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ይመ​ጣ​ልና፤
ያን​ጊ​ዜም ክፋ​ታ​ቸው ከየት እንደ ሆነ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ