የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 20

20
የሶ​ፋር ሁለ​ተኛ ንግ​ግር
1አሜ​ና​ዊ​ውም#ዕብ. “ናዕ​ማ​ታ​ዊው” ይላል። ሶፋር መለሰ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“እን​ደ​ዚህ እን​ደ​ም​ት​መ​ልስ አል​ጠ​ረ​ጠ​ር​ሁ​ህም ነበር፤
በዕ​ው​ቀ​ትም ከእኔ አት​ሻ​ልም።
3የት​ም​ህ​ር​ቴን ጥበብ ልን​ገ​ርህ፤ ስማኝ፤
የማ​ስ​ተ​ዋ​ሌም መን​ፈስ ይመ​ል​ስ​ል​ኛል።
4ሰው በም​ድር ላይ ከተ​ፈ​ጠረ፥ ከድሮ ዘመን ጀምሮ፥
በአ​ን​ተስ ዘመን እን​ደ​ዚህ ያለ ነገር ታው​ቃ​ለ​ህን?
5የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የው​ድ​ቀት ምል​ክት” ይላል። ነው፥
የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።
6መባው ወደ ሰማይ ቢወጣ፥
መሥ​ዋ​ዕ​ቱም እስከ ደመና ቢደ​ርስ፥
7እነሆ ተደ​ላ​ድ​ያ​ለሁ በሚ​ል​በት ጊዜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠ​ፋል።
የሚ​ያ​ው​ቁ​ትም ወዴት ነው? ይላሉ።
8እንደ ሕልም ይበ​ር​ራል፤ እር​ሱም አይ​ገ​ኝም፤
ሲነ​ጋም እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ እንደ ሌሊት ራእይ ይሰ​ደ​ዳል።
9ዐይን አየ​ችው፤ ነገር ግን ዳግ​መኛ አታ​የ​ውም፤
ስፍ​ራ​ው​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ው​ቀ​ውም።
10የተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ልጆ​ቹን ያጠ​ፋሉ፤
እጆ​ቹም የኀ​ዘን እሳ​ትን ያቀ​ጣ​ጥ​ላሉ።
11ጭን​ቀት በአ​ጥ​ን​ቶቹ ሞል​ቶ​አል፤
ነገር ግን ሕማሙ ከእ​ርሱ ጋር በመ​ሬት ውስጥ ይተ​ኛል።
12“ክፋት በአፉ ውስጥ ብት​ጣ​ፍ​ጠው፤
ከም​ላ​ሱም በታች ቢሰ​ው​ራት፥
13ቢጠ​ብ​ቃ​ትም፥ ባይ​ተ​ዋ​ትም፤
በጕ​ሮ​ሮ​ውም መካ​ከል ቢይ​ዛት፥
መብሉ በአ​ን​ጀቱ ውስጥ ይገ​ላ​በ​ጣል፤
14ፈጽሞ ራሱን መር​ዳት አይ​ች​ልም።
የእ​ፉ​ኝ​ትም መርዝ ከከ​ን​ፈሩ በታች አለ።
15በዐ​መፅ የሚ​ሰ​በ​ሰብ ሀብ​ትም ይጠ​ፋል፤
የሞት መል​አ​ክም ከቤቱ ውስጥ እያ​ዳፋ ያወ​ጣ​ዋል።
16የእ​ባ​ብን መርዝ ይጠ​ባል፤
የእ​ፉ​ኝ​ትም ምላስ ይገ​ድ​ለ​ዋል።
17የመ​ን​ጋ​ዎ​ቹ​ንም ጥጆች፥
የማ​ሩ​ንና የቅ​ቤ​ው​ንም ፈሳሽ አይ​መ​ለ​ከ​ትም።
18ለማ​ይ​ቀ​ም​ሰው፥ ለማ​ይ​ታ​ኘ​ክና ለማ​ይ​ዋጥ ሀብት
በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማል።
19የደ​ካ​ሞ​ችን ቤቶች አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፤
ያል​ሠ​ራ​ው​ንም ቤት በዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።
20ለን​ብ​ረቱ ጥበቃ የለ​ውም፤
የወ​ደ​ደ​ው​ንም ነገር አያ​ገ​ኝም።
21ለሀ​ብቱ ትርፍ የለ​ውም፤
ስለ​ዚህ በረ​ከቱ አት​ከ​ና​ወ​ን​ለ​ትም።
22በጠ​ገበ ጊዜ ይጨ​ነ​ቃል፤
መከ​ራም ሁሉ ያገ​ኘ​ዋል።
23“ሆዱን ቢያ​ጠ​ግብ፥
የመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍት ይጨ​መ​ር​በ​ታል፤
የሕ​ማ​ሙም ሥቃይ ይጸ​ና​በ​ታል።
24ከሰ​ይ​ፍም ኀይል አያ​መ​ል​ጥም፤
የና​ስም ቀስት ይወ​ጋ​ዋል።
25ቀስ​ቱም በሥ​ጋው ውስጥ ያል​ፋል።
ክፉም ነገር በሰ​ው​ነቱ ይመ​ላ​ለ​ሳል፤
ፍር​ሀ​ትም ይወ​ድ​ቅ​በ​ታል።
26ጨለማ ሁሉ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤
ዕፍ የማ​ይ​ባል እሳ​ትም ይበ​ላ​ዋል፤
እን​ግ​ዳም ቤቱን ያጠ​ቃ​ዋል።
27ሰማይ ኀጢ​ኣ​ቱን ይገ​ል​ጥ​በ​ታል፤
ምድ​ርም በእ​ርሱ ላይ ትነ​ሣ​ለች።
28ጥፋ​ትም ቤቱን ወደ ፍጻሜ ያመ​ጣ​ታል።
የቍጣ ቀንም ትመ​ጣ​በ​ታ​ለች።
29ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው እድል ፋን​ታው፥
ከሚ​ያ​የው ከፈ​ጣ​ሪ​ውም የተ​መ​ደበ ርስቱ ይህ ነው።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ