የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 1

1
ኢዮብ እንደ ተፈ​ተነ
1አው​ስ​ጢድ#ዕብ. “ዖፅ” ይላል። በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር። 2ሰባ​ትም ወን​ዶች፥ ሦስ​ትም ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት። 3ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።
4ወን​ዶች ልጆ​ቹም ሄደው በየ​ተራ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ቤት ግብዣ ያደ​ርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይወ​ስ​ዱ​አ​ቸው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ይበ​ሉና ይጠጡ ነበር። 5የግ​ብ​ዣ​ውም ቀኖች በተ​ፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዮብ ይል​ክና ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ነበር፤ በማ​ለ​ዳም ገሥ​ግሦ፦ ስለ ልጆቹ በቍ​ጥ​ራ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ አንድ ወይ​ፈን ስለ ነፍ​ሳ​ቸው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ ኢዮብ፥ “ምና​ል​ባት ልጆቼ በል​ባ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ ነገር ያስቡ ይሆ​ናል” ይል ነበ​ርና።
6ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት#ዕብ. “የአ​ም​ላክ ልጆች” ይላል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም መጡ፤ ሰይ​ጣ​ንም ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ሰይ​ጣ​ንም፥ “ምድ​ርን ሁሉ ዞር​ሁ​አት፥ ከሰ​ማይ በታ​ችም ተመ​ላ​ለ​ስ​ሁና መጣሁ።” ብሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መለሰ። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ የም​ታ​ስ​በው ነገር እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቅ! በም​ድር ላይ እንደ እርሱ ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ሰው የለ​ምና።” 9ሰይ​ጣ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብሎ መለሰ፥ “በውኑ ኢዮብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​መ​ል​ከው በከ​ንቱ ነውን? 10አንተ ቤቱን በው​ስ​ጥም በው​ጭም፥ በዙ​ሪ​ያው ያለ​ው​ንም ሁሉ አል​ሞ​ላ​ህ​ለ​ት​ምን? የእ​ጁ​ንም ሥራ ባር​ከ​ህ​ለ​ታል፥ ከብ​ቱ​ንም በም​ድር ላይ አብ​ዝ​ተ​ህ​ለ​ታል። 11ነገር ግን እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ ያለ​ውን ሁሉ ዳስስ፤ በእ​ው​ነት በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ብ​ሃል።” 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “እነሆ፥ ለእ​ርሱ ያለ​ውን ሁሉ በእ​ጅህ ሰጠ​ሁህ፥ ነገር ግን በእ​ርሱ ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ” አለው። ሰይ​ጣ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ።
የኢ​ዮብ ንብ​ረት እንደ ጠፋና ልጆቹ እንደ ሞቱ
13አንድ ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ የኢ​ዮብ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች በታ​ላቅ ወን​ድ​ማ​ቸው ቤት ይበ​ሉና የወ​ይን ጠጅ ይጠጡ ነበር። 14መል​እ​ክ​ተ​ኛም ወደ ኢዮብ መጥቶ፥ “ጥምድ በሬ​ዎ​ችህ እርሻ ያርሱ ነበር፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ሴቶች አህ​ዮ​ችህ ይሰ​ማሩ ነበር፤ 15ማራ​ኪ​ዎ​ችም#ዕብ. “የሳባ ሰዎች” ይላል። መጥ​ተው ወሰ​ዱ​አ​ቸው፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ” አለው። 16እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሌላ መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፦ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “እሳት ከሰ​ማይ ወደ​ቀች፥ በጎ​ች​ህ​ንም አቃ​ጠ​ለች፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ህ​ንም በላች፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።” 17እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሦስ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ፈረ​ሰ​ኞች#ዕብ. “ከለ​ዳ​ው​ያን” ይላል። በሦ​ስት ረድፍ ከብ​በው ግመ​ሎ​ችን ማር​ከው ወሰዱ፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።” 18እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር አራ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችህ በታ​ላቅ ወን​ድ​ማ​ቸው ቤት ሲበ​ሉና የወ​ይን ጠጅ ሲጠጡ፥ 19እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከም​ድረ በዳ ድን​ገት መጥቶ ቤቱን በአ​ራት ማዕ​ዘኑ መታው፥ ቤቱም በብ​ላ​ቴ​ኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነ​ር​ሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”
20ኢዮ​ብም ተነሣ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም ቀደደ፥ ራሱ​ንም ተላጨ፥ በም​ድ​ርም ላይ ተደ​ፍቶ ሰገደ፤ 21እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ራቁ​ቴን ወጥ​ቻ​ለሁ፥ ራቁ​ቴ​ንም ወደ ምድር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወደ​ዚ​ያው እመ​ለ​ሳ​ለሁ” ይላል። እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጠ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነሣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ፈቀደ ሆነ#“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ፈቀደ ሆነ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ብ​ሔር ስም የተ​ባ​ረከ ይሁን።” 22በዚ​ህም በደ​ረ​ሰ​በት ሁሉ ኢዮብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​በ​ደ​ለም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስን​ፍ​ናን አል​ሰ​ጠም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}