የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 2

2
ሰይ​ጣን ኢዮ​ብን እንደ ገና እንደ ፈተ​ነው
1ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት መጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ፥ ሰይ​ጣን ደግሞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ሰይ​ጣ​ንም፥ “ከሰ​ማይ በታች በም​ድር ላይ ዞርሁ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ተመ​ላ​ለ​ስሁ” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መለሰ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “በባ​ሪ​ያዬ በኢ​ዮብ ላይ እን​ዲህ እን​ዳ​ታ​ስብ ተጠ​ን​ቀቅ፤ በም​ድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ገር፥ ጻድ​ቅና ንጹሕ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ከክ​ፋ​ትም ሁሉ የራቀ፥ ዳግ​መ​ኛም ቅን የሆነ ሰው የለ​ምና፤ አንተ ግን ሀብ​ቱን በከ​ንቱ አጠፋ ዘንድ ነገ​ር​ኸኝ።” 4ሰይ​ጣ​ንም መልሶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ቍር​በት ስለ ቍር​በት ነው፤ ሰው ያለ​ውን ሁሉ ስለ ሕይ​ወቱ ይሰ​ጣል። 5ነገር ግን አሁን እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ አጥ​ን​ቱ​ንና ሥጋ​ውን ዳስስ፤ በእ​ው​ነት በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ብ​ሃል” ብሎ መለሰ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “እነሆ፥ ሥጋ​ው​ንና አጥ​ን​ቱን በእ​ጅህ ሰጠ​ሁህ። ነገር ግን ሕይ​ወ​ቱን ተው።”
7ሰይ​ጣ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮ​ብ​ንም ከእ​ግሩ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው። 8ቍስ​ሉ​ንም ያክ​ክ​በት ዘንድ ገል ወሰደ፥ ከከ​ተ​ማም ወጥቶ በአ​መድ ላይ ተቀ​መጠ። 9ብዙ ወራ​ትም ካለፈ በኋላ ሚስቱ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “እስከ መቼ ትታ​ገ​ሣ​ለህ? 9 ‘ሀ’ ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጥቂት ወራት ደጅ እጠ​ና​ዋ​ለሁ፤ ዳግ​መ​ኛም መከ​ራ​ውን እታ​ገ​ሠ​ዋ​ለሁ፤ የቀ​ድ​ሞው ኑሬ​ዬ​ንም ተስፋ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ ትላ​ለ​ህን? 9 ‘ለ’ እን​ደ​ዚ​ህስ እን​ዳ​ትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም አጠ​ራ​ርህ ጠፋ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆቼም ሞቱ፥ ማኅ​ፀ​ኔም በምጥ ተጨ​ነቀ፥ በከ​ን​ቱም ደከ​ምሁ። 9 ‘ሐ’ አን​ተም በመ​ግ​ልና በትል ትኖ​ራ​ለህ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ትዛ​ብ​ራ​ለህ። 9 ‘መ’ እኔ ግን እየ​ዞ​ርሁ እቀ​ላ​ው​ጣ​ለሁ። ከአ​ንዱ መን​ደር ወደ አንዱ መን​ደር፥ ከአ​ንዱ ቤትም ወደ አንዱ ቤት እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከድ​ካ​ሜና በእኔ ላይ ካለ ችግ​ሬም ዐርፍ ዘንድ ፀሐይ እስ​ኪ​ገባ ድረስ እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስደ​ብና ሙት።”#ምዕ. 2 ከቍ. 9‘ሀ’ እስከ 9‘መ’ ያለው በዕብ. የለም። 10እርሱ ግን፦ ወደ እር​ስዋ ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰ​ነ​ፎች ሴቶች እንደ አን​ዲቱ ተና​ገ​ርሽ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መል​ካ​ሙን ተቀ​በ​ልን፥ ክፉ​ውን ነገ​ርስ አን​ታ​ገ​ሥ​ምን?” በዚህ በደ​ረ​ሰ​በት ሁሉ ኢዮብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በከ​ን​ፈሩ አል​በ​ደ​ለም።
ወዳ​ጆቹ ኢዮ​ብን ሊጐ​በ​ኙት እንደ መጡ
11ሦስ​ቱም የኢ​ዮብ ወዳ​ጆች ይህን የደ​ረ​ሰ​በ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰም​ተው ከየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነ​ር​ሱም ቴማ​ና​ዊው ንጉሥ ኤል​ፋዝ፥ አው​ኬ​ና​ዊው#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ሱሐ​ዊው” ይላል። መስ​ፍን በል​ዳ​ዶስ፥ አሜ​ና​ዊው#ዕብ. “ናዕ​ማ​ታዊ” ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሚኒ​አ​ንስ” ይላል። ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሊጐ​በ​ኙ​ትና ሊያ​ጽ​ና​ኑት በአ​ን​ድ​ነት ወደ እርሱ መጡ። 12ከሩ​ቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላ​ወ​ቁ​ትም፤ በታ​ላቅ ድም​ፅም ጮኸው አለ​ቀሱ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ። 13ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​መጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስ​ፈ​ሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ርሱ አንድ ቃል የሚ​ና​ገ​ረው አል​ነ​በ​ረም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ