የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 14

14
ስለ እስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከስ​ደት መመ​ለስ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን ይም​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ ይመ​ር​ጠ​ዋል፤ በሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ፤ መጻ​ተ​ኞ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ጋር ይጨ​መ​ራሉ። 2አሕ​ዛ​ብም ይዘው ወደ ስፍ​ራ​ቸው ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገ​ኖች ይካ​ፈ​ሏ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ያም ሀገር ይበ​ዛሉ፤ በዚ​ያም ወን​ዶች ባሮ​ችና ሴቶች ባሮች ይሆ​ናሉ። ማር​ከው የወ​ሰ​ዷ​ቸ​ውም ለእ​ነ​ርሱ ምር​ኮ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ የገ​ዙ​አ​ቸ​ውም ይገ​ዙ​ላ​ቸ​ዋል።
3በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኀ​ዘ​ን​ህና ከመ​ከ​ራህ፥ ከተ​ገ​ዛ​ህ​ለ​ትም ከጽኑ ባር​ነት ያሳ​ር​ፍ​ሃል። 4ይህ​ንም ሙሾ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ታነ​ሣ​ለህ፤#ግእዝ “የባ​ቢ​ሎ​ንን መን​ግ​ሥት ዙፋን ትወ​ስ​ዳ​ለህ” ይላል። እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፥ “አስ​ጨ​ናቂ እን​ዴት ዐረፈ! አስ​ገ​ባ​ሪም እን​ዴት ጸጥ አለ! 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን ቀን​በ​ርና የአ​ለ​ቆ​ችን ቀን​በር ሰብ​ሮ​አ​ልና። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት አሕ​ዛ​ብን ገር​ፎ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ ከቍ​ጣ​ውም መቅ​ሠ​ፍት አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ው​ምና። 7ምድ​ርም ሁሉ ዐርፋ በጸ​ጥታ ተቀ​ም​ጣ​ለች፤ እል​ልም ብላ​ለች። 8የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፦ አንተ ከተ​ዋ​ረ​ድህ ጀምሮ ማንም ይቈ​ር​ጠን ዘንድ አል​ወ​ጣ​ብ​ንም ብለው በአ​ንተ ደስ አላ​ቸው።
9“ሲኦ​ልም በመ​ም​ጣ​ትህ ልት​ገ​ና​ኝህ በታች ታወ​ከች፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ከዙ​ፋ​ና​ቸው ያስ​ነሡ፥ ምድ​ርን የገ​ዙ​አት አር​በ​ኞች ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንተ ላይ ተነሡ። 10እነ​ዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ተይ​ዘ​ሃል፤ እንደ እኛም ተቈ​ጥ​ረ​ሃል። 11ከክ​ብ​ርህ ወደ ሲኦል ወደ​ቅህ፤ በበ​ታ​ች​ህም ብል ተነ​ጥ​ፎ​አል፤ ትልም መደ​ረ​ቢ​ያህ ሆኖ​አል” ብለው ይመ​ል​ሱ​ል​ሃል።
12“አንተ በን​ጋት የሚ​ወጣ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ሆይ፥ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወደ​ቅህ! ወደ አሕ​ዛ​ብም መል​እ​ክ​ትን የላ​ክህ አንተ ሆይ፥ እን​ዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀ​ጠ​ቀ​ጥህ! 13አን​ተም በል​ብህ፦ ወደ ሰማይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ ዙፋ​ኔ​ንም ከሰ​ማይ ከዋ​ክ​ብት በላይ ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሰ​ሜ​ንም#ግእዝ “ደቡብ” ይላል። ዳርቻ በረ​ዣ​ዥም ተራ​ሮች ላይ እቀ​መ​ጣ​ለሁ፤ 14ከደ​መ​ና​ዎች ከፍታ በላይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ በል​ዑ​ልም እመ​ሰ​ላ​ለሁ አልህ። 15ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወ​ድ​ቃ​ለህ፤ ወደ ምድር ጥል​ቅም ትወ​ር​ዳ​ለህ። 16የሚ​መ​ለ​ከ​ቱ​ህም ይደ​ነ​ቃሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፦ በውኑ ምድ​ርን ያን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንም ያና​ወጠ፥ 17ዓለ​ሙን ሁሉ ባድማ ያደ​ረገ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ያፈ​ረሰ፥ ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ቤታ​ቸው ያል​ሰ​ደደ ሰው ይህ ነውን?
18“የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ በየ​ቤ​ታ​ቸው በክ​ብር አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል። 19አንተ ግን በጦር ተወ​ግ​ተው ወደ መቃ​ብር ከሚ​ወ​ርዱ ብዙ ሙታን ጋር እንደ ረከሰ ሬሳ በተ​ራ​ሮች ላይ ትጣ​ላ​ለህ። 20ንጹሕ እን​ዳ​ል​ሆ​ነና በደም እንደ ረከሰ ልብስ አን​ተም ንጹሕ አይ​ደ​ለ​ህም። ምድ​ሬን አጥ​ፍ​ተ​ሃ​ልና፥ ሕዝ​ቤ​ንም ገድ​ለ​ሃ​ልና ክፉ ዘር አንተ እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ኖ​ርም። 21እን​ዳ​ይ​ነ​ሡም፥ ምድ​ር​ንም እን​ዳ​ይ​ወ​ርሱ፥ የዓ​ለ​ሙ​ንም ፊት በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞሉ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው በደል ይገ​ድ​ሉ​አ​ቸው ዘንድ ልጆ​ች​ህን አዘ​ጋጅ።” 22“በእ​ነ​ርሱ ላይ እነ​ሣ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ስም​ንና ቅሬ​ታን፥ ዘር​ንና ትው​ል​ድ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 23“ባቢ​ሎ​ንን የወ​ፎች መኖ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ትሆ​ና​ለች፤ በጥ​ፋ​ትም እንደ ረግ​ረግ ጭቃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
በአ​ሦር ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
24የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ምሎ​አል፥ “እንደ ተና​ገ​ርሁ በእ​ር​ግጥ ይሆ​ናል፤ እንደ መከ​ር​ሁም እን​ዲሁ ይጸ​ናል። 25አሦ​ርን በም​ድሬ ላይ እሰ​ብ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በተ​ራ​ራ​ዬም ላይ እረ​ግ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ቀን​በ​ሩም ከእ​ነ​ርሱ ላይ ይነ​ሣል፤ ሸክ​ሙም ከጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይወ​ገ​ዳል።” 26በም​ድር ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በው ዐሳብ ይህ ነው፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ የተ​ዘ​ረ​ጋች እጅ ይህች ናት። 27ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን መክ​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር የሚ​መ​ልስ ማን ነው? የተ​ዘ​ረ​ጋች እጁ​ንስ የሚ​መ​ል​ሳት ማን ነው?
በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
28ንጉሡ አካዝ በሞ​ተ​በት ዓመት ይህ ነገር ሆነ። 29ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ። 30ድሆ​ችም በው​ስ​ጣ​ችሁ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ድሆች ሰዎ​ችም በሰ​ላም ያር​ፋሉ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ረኃብ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የቀ​ሩት ያል​ቃሉ። 31እና​ንተ የከ​ተ​ሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እና​ን​ተም ከተ​ሞች ሆይ፥ ደን​ግጡ፥ ጩኹም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ፥ ሁላ​ች​ሁም ቀል​ጣ​ች​ኋል፤ ጢስ ከሰ​ሜን ይወ​ጣ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሩ​ምና።
32የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ