የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 13

13
ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ትን​ቢት እንደ ተና​ገረ
1የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ያየው ራእይ።
2ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምል​ክ​ትን አቁሙ፤ ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ከፍ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ አለ​ቆች በእጅ ጥቀሱ። በሮ​ች​ንም ክፈቱ። 3እኔ አዝዤ ቅዱ​ሳ​ኔን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ኀያ​ላ​ኔ​ንም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደስ እያ​ላ​ቸ​ውም ይመ​ጣሉ፤ ቍጣ​ዬ​ንም ይፈ​ጽ​ማሉ፤ ያዋ​ር​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልም። 4በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተ​ሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሥ​ታ​ትና የአ​ሕ​ዛብ ድም​ፅም አለ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተዋ​ጊ​ዎች አሕ​ዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና የቍ​ጣው ሠራ​ዊት ዓለ​ምን ያጠ​ፉ​አት ዘንድ ከሩቅ ሀገር ከሰ​ማይ ዳርቻ ይመ​ጣሉ።
6የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና አል​ቅሱ፤ ጥፋ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይመ​ጣል። 7ስለ​ዚህ እጅ ሁሉ ትዝ​ላ​ለች፤ ሰውም ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ 8ሽማ​ግ​ሎች ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይገ​ዳ​ደ​ላሉ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እርስ በር​ሳ​ቸው ይላ​ቀ​ሳሉ” ይላል። ይደ​ነ​ቃሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ እሳት ይን​በ​ለ​በ​ላል።
9እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ባድማ ሊያ​ደ​ርግ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ዋ​ንም ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ሊያ​ጠፋ በመ​ዓ​ትና በጽኑ ቍጣ ተሞ​ልቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ይመ​ጣል። 10የሰ​ማ​ይም ከዋ​ክ​ብ​ትና ኦሪ​ዎን፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትም ሁሉ ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም፤ ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ ትጨ​ል​ማ​ለች፤ ጨረ​ቃም በብ​ር​ሃኑ አያ​በ​ራም። 11በዓ​ለም ሁሉ ላይ ክፋ​ትን አዝ​ዛ​ለሁ፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ኀጢ​አት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም ኵራት እሽ​ራ​ለሁ፤ የጨ​ካ​ኞ​ቹ​ንም ኵራት አዋ​ር​ዳ​ለሁ። 12የተ​ረ​ፉ​ትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከ​በሩ ይሆ​ናሉ፤ ሰውም ከሰ​ን​ፔር ዕንቍ ይልቅ የከ​በረ ይሆ​ናል። 13ስለ​ዚህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማ​ያት ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ምድ​ርም ከመ​ሠ​ረቷ ትና​ወ​ጣ​ለች። 14የተ​ረ​ፉ​ትም ሁሉ እንደ ተባ​ረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆ​ናሉ። የሚ​ሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ውም የለም፤ እን​ዲ​ሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል። 15የተ​በ​ተ​ኑት ሁሉ ይሞ​ታሉ፤ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​ትም ሁሉ በጦር ይወ​ድ​ቃሉ። 16ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ቸው ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ቤቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛሉ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያስ​ነ​ው​ራሉ።
17እነሆ፥ ብር የማ​ይ​ሹ​ትን፥ ወር​ቅም የማ​ያ​ም​ራ​ቸ​ውን ሜዶ​ና​ው​ያ​ንን በእ​ና​ንተ ላይ አስ​ነ​ሣ​ለሁ። 18ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ጐበ​ዞ​ችን ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም አይ​ም​ሩም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አይ​ራ​ሩም። 19የመ​ን​ግ​ሥ​ታት ክብር፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም የት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ትም​ክ​ሕት የሆ​ነች ባቢ​ሎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ትሆ​ና​ለች። 20ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባት አይ​ገ​ኝም፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ሰው አይ​ኖ​ር​ባ​ትም፤ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም በእ​ርሷ አያ​ል​ፉም፤ እረ​ኞ​ችም በው​ስ​ጥዋ አያ​ር​ፉም። 21በዚ​ያም የም​ድረ በዳ አራ​ዊት ያር​ፋሉ፤ ጕጕ​ቶ​ችም በቤ​ቶ​ቻ​ቸው ይሞ​ላሉ፤ ሰጎ​ኖ​ችም በዚያ ይኖ​ራሉ፤ በዚ​ያም አጋ​ን​ንት ይዘ​ፍ​ናሉ። 22ተኵ​ላ​ዎ​ችም በዚያ ያድ​ራሉ፤ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም በሚ​ያ​ማ​ምሩ አዳ​ራ​ሾ​ቻ​ቸው ይዋ​ለ​ዳሉ፤ ይህም ሁሉ ፈጥኖ ይሆ​ናል፤ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ