ትንቢተ ኢሳይያስ 12
12
የምስጋና መዝሙር
1በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና#ዕብ. “አጽናንተኸኛልና” ይላል። አመሰግንሃለሁ። 2እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።” 3ውኃውንም ከሕይወት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። 4በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ። 5ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ስም ዘምሩ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ። 6አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና።”
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 12: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ