1
ትንቢተ ኢሳይያስ 12:2
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 12:3
ውኃውንም ከሕይወት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 12:5
ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ስም ዘምሩ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 12:4
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 12:1
በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 12:6
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና።”
Home
Bible
Plans
Videos