ትንቢተ ኢሳይያስ 15
15
ስለ ሞዓብ ጥፋት
1ስለ ሞዓብ የተነገረ ቃል። ሞዓብ በሌሊት ትጠፋለች፤ የሞዓብም ምሽግ በሌሊት ይፈርሳል። 2ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል። 3በየመንገድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየሰገነቶችዋም አልቅሱ፤ በየአደባባዮችዋም እንባን እጅግ እያፈሰሳችሁ ወዮ በሉ። 4ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰማል፤ ስለዚህ የሞዓብ ወገብ ይታመማል። 5ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል። 6የኔምሬም ውኃ ይነጥፋል፤ ሣሯም ይደርቃል፤ በውስጧም ልምላሜ አይገኝም። 7ስለዚህ ሞዓብ ይድናልን? ዐረባውያንን ወደ ሸለቆው አመጣቸዋለሁና፤ እነርሱም ይወስዷታል። 8ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ኢሊም ጕድጓድ ደረሰ። 9የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ በዲሞን ላይ ዐረባውያንን አመጣለሁና፤ የሞዓብንና የአርያልን ዘር፥ ከኤዶምያስም የተረፉትን ወስጄ እንደ አራዊት በምድር ላይ እሰድዳቸዋለሁ።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 15: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ