ትንቢተ ኢሳይያስ 16
16
1የጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ምድረ በዳ አይደለችምን?#ምዕ. 16 ቍ. 1 በዕብ. “በምድር ላይ ለሰለጠነው አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ሰደዱ” ይላል። 2ጫጩቶችዋን አሳድጋ እንደ ተወች ወፍ ሆናለችና፤ የሞዓብ ሴት ልጅም እንደ ሰባ የበግ ጠቦት ሆነች። 3አርኖንም በምትኖርበት ምሽግ መጠለያን ትሠራ ዘንድ ብዙ ትመክራለች፤ በቀትር ጊዜ እንደ ሌሊት ደንግጠው ይሸሻሉ፤ ወደ እናንተም አታስገቡአቸው። 4ከሚከቧችሁ ጋር ጠላቶች እንዳይሆኗችሁ ከሞዓብ የተሰደዱትን ከእናንተ ጋር አታስቀምጡ፤ ሰልፈኞች አልቀዋልና፤ በሀገሪቱ ሁሉ የነበረውም አለቃ ጠፍቶአልና።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይቀመጡ ፤ በሚያሳድዱሽ ፊት ከለላ ይሆኑሻል ፤ አርበኞችሽ ዐልቀዋልና ይጨቁን የነበረውም ገዢ ከምድር ሁሉ ጠፍትዋልና” ይላል። 5ዙፋን በምሕረት ይጸናል፥ በዚያም ላይ በዳዊት ቤት ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያፋጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል፤ ይፈርዳልም።
6የሞዓብን ትዕቢትና እጅግ መኵራቱን ሰምተናል፤ ትዕቢቱንም አስወገድሁ፤ ጥንቈላህ እንዲህ አይደለምና፥ እንዲህም አይደለም፤ 7ሞዓብ ዋይ በሉ፤ ሁሉም በሞዓብ ዋይ ይላሉና፤ በዴሴት የሚኖሩም አያመልጡም፤ ጠብን ያጭራሉ፤ ያፍራሉም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ነገር ግን በሴት ከተማ ስለሚኖሩ ተጠንቀቁ ፤ አታፍሩምም” ይላል። 8የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፤ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር። 9ስለዚህ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ ዛፎችሽ ወድቀዋል፤ የዛፍሽን ፍሬና የወይንሽን መከር እረግጣለሁ፤ ተክሎችሽ ሁሉ ይወድቃሉ። 10ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና። 11ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ መሰንቆ ትጮኻለች። አጥንቶችም እንደ ተመረገ ግድግዳ ይሆናሉ። 12ለኀፍረት ይሆንብሃል፤ ሞዓብ በመሠዊያዎችዋ ደክማለችና፤ ለጸሎትም ወደ ጣዖቶችዋ ትሄዳለች፤ ሊያድኑአትም አይችሉም። 13እግዚአብሔር በሞዓብ ላይ በድሮ ዘመን የተናገረው ነገር ይህ ነው። 14አሁንም እንዲህ እላለሁ፤ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብር ከብዙ ሀብትዋ ጋር ይዋረዳል፤ በቍጥርም ጥቂት ይቀራል፤ ክብርዋም አይገኝም።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 16: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ