የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 15

15
ስለ ሞዓብ ጥፋት
1ስለ ሞዓብ የተ​ነ​ገረ ቃል። ሞዓብ በሌ​ሊት ትጠ​ፋ​ለች፤ የሞ​ዓ​ብም ምሽግ በሌ​ሊት ይፈ​ር​ሳል። 2ለራ​ሳ​ችሁ እዘኑ፤ ጣዖ​ታ​ች​ሁና መሠ​ዊ​ያ​ችሁ ያሉ​ባት ዲቦን ትጠ​ፋ​ለ​ችና፤ ወደ​ዚ​ያም ወጥ​ታ​ችሁ በሞ​ዓብ ናባው አል​ቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆ​ናል፤ ክን​ድም ሁሉ ይቈ​ረ​ጣል። 3በየ​መ​ን​ገ​ድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየ​ሰ​ገ​ነ​ቶ​ች​ዋም አል​ቅሱ፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ዋም እን​ባን እጅግ እያ​ፈ​ሰ​ሳ​ችሁ ወዮ በሉ። 4ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ጮኹ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ የሞ​ዓብ ወገብ ይታ​መ​ማል። 5ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮ​ኻ​ለች፤ ለል​ቧም ይረ​ዳ​ታል፤ እስከ ሴጎ​ርም ድረስ ብቻ​ዋን ታለ​ቅ​ሳ​ለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉ​ሒት ዐቀ​በት ትጮ​ኻ​ለች። በአ​ሮ​ሜ​ዎን መን​ገ​ድም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ይጮ​ኻ​ሉም፥ ጥፋ​ትና መና​ወ​ጥም ይሆ​ናል። 6የኔ​ም​ሬም ውኃ ይነ​ጥ​ፋል፤ ሣሯም ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጧም ልም​ላሜ አይ​ገ​ኝም። 7ስለ​ዚህ ሞዓብ ይድ​ና​ልን? ዐረ​ባ​ው​ያ​ንን ወደ ሸለ​ቆው አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ስ​ዷ​ታል። 8ጩኸት የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅ​ሶ​ዋም ወደ ኤግ​ላ​ይ​ምና ወደ ኢሊም ጕድ​ጓድ ደረሰ። 9የዲ​ሞ​ንም ውኃ ደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በዲ​ሞን ላይ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ የሞ​ዓ​ብ​ንና የአ​ር​ያ​ልን ዘር፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም የተ​ረ​ፉ​ትን ወስጄ እንደ አራ​ዊት በም​ድር ላይ እሰ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ