የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 7

7
1ከመ​ል​ካም ሽቱ መል​ካም ስም፥ ከመ​ወ​ለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻ​ላል። 2ወደ ግብዣ ቤትም ከመ​ሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻ​ላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያ​ውም የሆነ ይህን መል​ካም ነገር በልቡ ያኖ​ረ​ዋል። 3ከሣቅ ኀዘን ይሻ​ላል፥ ከፊት ኀዘን የተ​ነሣ ልብ ደስ ይሰ​ኛ​ልና። 4የጠ​ቢ​ባን ልብ በል​ቅሶ ቤት ነው፤ የሰ​ነ​ፎች ልብ ግን በደ​ስታ ቤት ነው። 5ለሰው የሰ​ነ​ፎ​ችን ዘፈን ከሚ​ሰማ ይልቅ የጠ​ቢ​ባ​ንን ተግ​ሣጽ መስ​ማት ይሻ​ለ​ዋል። 6ከድ​ስት በታች እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል እሾህ ድምፅ የሰ​ነፍ ሣቅ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። 7ግፍ ጠቢ​ብን ያሳ​ብ​ደ​ዋል፥ የል​ቡ​ንም ትዕ​ግ​ሥት ያጠ​ፋ​ዋል። 8የነ​ገር ፍጻሜ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ይሻ​ላል፤ ታጋ​ሽም ከልብ ትዕ​ቢ​ተኛ ይሻ​ላል። 9በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።
10ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለ​ፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አት​ና​ገር፤ የዚ​ህን ነገር በጥ​በብ አት​ጠ​ይ​ቅ​ምና።
11ጥበብ ከር​ስት ጋር መል​ካም ነው፤ ፀሓ​ይ​ንም ለሚ​ያዩ ሰዎች ትር​ፍን ይሰ​ጣል። 12የጥ​በብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻ​ላል፤ የጥ​በ​ብ​ንም ዕው​ቀት ማብ​ዛት ገን​ዘብ ላደ​ረ​ጋት ሕይ​ወ​ትን ትሰ​ጠ​ዋ​ለች። 13የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ተመ​ል​ከት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠማማ ያደ​ረ​ገ​ውን ማን ሊያ​ቀ​ናው ይች​ላል? 14በመ​ል​ካም ቀን ደስ ይበ​ልህ ፤ በክ​ፉም ቀን ተመ​ል​ከት፤ ሰው ከእ​ርሱ በኋላ መር​ምሮ ምንም እን​ዳ​ያ​ገኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ንም ያንም እን​ደ​ዚያ ሠራ።
15ጻድቅ በጽ​ድቁ ሲጠፋ፥ ኃጥ​እም በክ​ፋቱ ሲኖር፥ ይህን ሁሉ በከ​ንቱ ዘመኔ አየሁ። 16እጅግ ጻድቅ አት​ሁን፥ እጅ​ግም ጠቢብ አት​ሁን፥ እን​ዳ​ት​በ​ድል። 17እጅግ ክፉ አት​ሁን፥ እል​ከ​ኛም አት​ሁን፥ ያለ ጊዜህ እን​ዳ​ት​ሞት። 18ይህን ብት​ይዝ ለአ​ንተ መል​ካም ነው፤ በዚ​ህም እጅ​ህን አታ​ር​ክስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ከሁሉ ይወ​ጣ​ልና።
19በከ​ተማ ከሚ​ኖሩ ዐሥር ገዢ​ዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢ​ብን ትረ​ዳ​ዋ​ለች። 20በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና። 21አገ​ል​ጋ​ይህ ሲረ​ግ​ምህ እን​ዳ​ት​ሰማ በሚ​ጫ​ወ​ቱ​በት ቃል ሁሉ ልብ​ህን አት​ጣል። 22ብዙ ጊዜ ያበ​ሳ​ጭ​ሃ​ልና፤ በብዙ መን​ገ​ድም ልብ​ህን ያስ​ከ​ፋ​ታ​ልና፥ አንተ ደግሞ ሌሎ​ችን እንደ ረገ​ምህ ታው​ቃ​ለ​ህና። 23ይህን ሁሉ በጥ​በብ ፈተ​ንሁ፥ ጠቢ​ብም እሆ​ና​ለሁ አልሁ፥ እር​ስዋ ግን ከእኔ ራቀች። 24ርቃና እጅግ ጠልቃ ሳለች መር​ምሮ የሚ​ያ​ገ​ኛት ማን ነው? 25አው​ቅና እመ​ረ​ምር ዘንድ ጥበ​ብ​ንና የነ​ገ​ሩን ሁሉ መደ​ም​ደ​ሚያ እፈ​ልግ ዘንድ፥ የክ​ፉ​ዎ​ች​ንም ስን​ፍ​ናና ዕብ​ደት አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ። 26እኔም ከሞት ይልቅ የመ​ረ​ረች ነገ​ርን አገ​ኘሁ፤ እር​ስ​ዋም ልብዋ ወጥ​መ​ድና መረብ የሆነ፥ በእ​ጆ​ች​ዋም ማሰ​ሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደግ የሆነ ከእ​ርሷ ያመ​ል​ጣል። ኀጢ​አ​ተኛ ግን ይጠ​መ​ድ​ባ​ታል። 27እነሆ፥ ይህን ነገር አገ​ኘሁ ይላል ሰባ​ኪው፥ መደ​ም​ደ​ሚ​ያን ለማ​ግ​ኘት አን​ዲ​ቱን በአ​ን​ዲቱ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ መደ​ም​ደ​ሚያ እደ​ርስ ዘንድ ብመ​ረ​ምር፥ 28ነፍሴ የፈ​ለ​ገ​ች​ውን አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ከሺህ ወን​ዶች አንድ አገ​ኘሁ፥ ከእ​ነ​ዚያ ሁሉ መካ​ከል ግን አን​ዲት ሴት አላ​ገ​ኘ​ሁም። 29እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጊ​ዜው ሰዎ​ችን ቅኖች አድ​ርጎ እንደ ሠራ​ቸው እነሆ፥ ይህን ብቻ አገ​ኘሁ፥ እነ​ርሱ ግን ብዙ ዕው​ቀ​ትን ይሻሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ