1
መጽሐፈ መክብብ 7:9
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
በመንፈስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን፥ ቍጣ በሰነፎች ብብት ያርፋልና።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መክብብ 7:14
በመልካም ቀን ደስ ይበልህ ፤ በክፉም ቀን ተመልከት፤ ሰው ከእርሱ በኋላ መርምሮ ምንም እንዳያገኝ እግዚአብሔር ይህንም ያንም እንደዚያ ሠራ።
3
መጽሐፈ መክብብ 7:8
የነገር ፍጻሜ ከመጀመሪያው ይሻላል፤ ታጋሽም ከልብ ትዕቢተኛ ይሻላል።
4
መጽሐፈ መክብብ 7:20
በምድር ላይም መልካምን የሚሠራ ኀጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ ሰው አይገኝምና።
5
መጽሐፈ መክብብ 7:12
የጥበብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻላል፤ የጥበብንም ዕውቀት ማብዛት ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትሰጠዋለች።
6
መጽሐፈ መክብብ 7:1
ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።
7
መጽሐፈ መክብብ 7:5
ለሰው የሰነፎችን ዘፈን ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል።
8
መጽሐፈ መክብብ 7:2
ወደ ግብዣ ቤትም ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ ይህን መልካም ነገር በልቡ ያኖረዋል።
9
መጽሐፈ መክብብ 7:4
የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።
Home
Bible
Plans
Videos