የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 8

8
ንጉ​ሥን ስለ ማክ​በር
1ዐዋ​ቂ​ዎ​ችን ማን ያው​ቃ​ቸ​ዋል? ቃላ​ቸ​ው​ንስ መተ​ር​ጐም የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበ​ራ​ለች፥ በፊ​ቱም ኀፍ​ረት የሌ​ለው ሰው ይጠ​ላል። 2ልጄ ሆይ፥ የን​ጉ​ሥን አፍ ጠብቅ፤ ለመ​ሐላ ቃልም አት​ቸ​ኩል። 3የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ጋ​ልና ከፊቱ ሂድ፥ በክፉ ነገ​ርም አት​ቁም፥ 4ንጉሥ እንደ መሆኑ ኀይል አለ​ውና፤ ይህ​ንስ ለምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ማን ይለ​ዋል? 5ትእ​ዛ​ዝን የሚ​ጠ​ብቅ ክፉን ነገር አያ​ው​ቅም፤ የጠ​ቢ​ብም ልብ የፍ​ር​ድን ጊዜ ያው​ቃል። 6የሰው ዕው​ቀት በእ​ርሱ ላይ ታላቅ ስለ ሆነ ለነ​ገር ሁሉ ጊዜና ፍርድ አለ​ውና። 7የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ እን​ዴ​ትስ እን​ደ​ሚ​ሆን የሚ​ነ​ግ​ረው ማን ነው? 8መን​ፈ​ስን ለማ​ስ​ቀ​ረት በመ​ን​ፈሱ ላይ ሥል​ጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞ​ትም ቀን ሥል​ጣን የለ​ውም፤ በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ ስን​ብት የለም፥ ኀጢ​አ​ትም ሠሪ​ውን አያ​ድ​ነ​ውም። 9ይህን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት አየሁ፥ ከፀ​ሓ​ይም በታች ወደ ተደ​ረ​ገው ሥራ ሁሉ ልቤን ሰጠሁ፤ ሰውም ሰውን ለመ​ጕ​ዳት ገዥ የሚ​ሆ​ን​በት ጊዜ አለ።
የክ​ፉና የደግ ሰው ሁኔታ
10እን​ዲ​ሁም ያን​ጊዜ ኃጥ​ኣን ወደ ጽኑ መቃ​ብር ሲገቡ አየሁ፥ ከቅ​ድ​ስት ስፍ​ራም ወጥ​ተው ተለዩ፤ እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማዋ ተመ​ሰ​ገኑ፥ እን​ዲህ ሠር​ተ​ዋ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። 11ክፉን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ወገን ፈጥኖ ክር​ክ​ርን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለ​ምና፤ ስለ​ዚህ የሰው ልጆች ልብ በእ​ነ​ርሱ ክፉን ለመ​ሥ​ራት ጠነ​ከረ። 12የበ​ደለ ከጥ​ንት ጀምሮ ከዚ​ያም በፊት ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ጓል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ፈ​ሩት በፊ​ቱም ለሚ​ፈ​ሩት ደኅ​ን​ነት እን​ዲ​ሆን አው​ቃ​ለ​ሁና፤ 13ለኃ​ጥእ ግን ደኅ​ን​ነት የለ​ውም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አይ​ፈ​ራ​ምና ዘመኑ እንደ ጥላ አት​ረ​ዝ​ምም።
14ከፀ​ሓይ በታች በም​ድር የሚ​ደ​ረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃ​ጥ​ኣን የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸው ጻድ​ቃን አሉ፥ ለጻ​ድ​ቃ​ንም የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ላ​ቸው ኃጥ​ኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ። 15ከሚ​በ​ላ​ውና ከሚ​ጠ​ጣው፥ ደስም ከሚ​ለው በቀር ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ሌላ መል​ካም ነገር የለ​ው​ምና እኔ ደስ​ታን አመ​ሰ​ገ​ንሁ፤ ይህም ከፀ​ሓይ በታች ከድ​ካሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ለእ​ርሱ የሰ​ጠው ነው።
16ጥበ​ብን አውቅ ዘንድ በም​ድር የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊት እን​ቅ​ል​ፍን በዐ​ይኑ የሚ​ያይ የለ​ምና። 17ከፀ​ሓ​ይም በታች የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ሥራ መር​ምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እን​ዳ​ይ​ቻ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈ​ልግ እጅግ ቢደ​ክም መር​ምሮ አያ​ገ​ኘ​ውም፤ ደግ​ሞም ጠቢብ ሰው፥ “ይህን ዐወ​ቅሁ” ቢል እርሱ ያገ​ኘው ዘንድ አይ​ች​ልም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ