የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 26

26
1በረዶ በበጋ ዝናብም በመከር እንደማይፈልግ ሁሉ፥
እንዲሁም ለሞኝ ክብር አይገባውም።
2ወዲያና ወዲህ እንደሚበርር ድንቢጥ ወይም ጨረባ፥
እንዲሁም ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም።
3አለንጋ ለፈረስ፥ ልጓም ለአህያ፥
በትርም ለሞኝ ጀርባ ነው።
4አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል
ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ አትመልስለት።
5ለራሱ ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው
ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት።
6በሞኝ አማካኝነት መልእክት የሚልክ፥
እግሮቹን ይቈርጣል፥ ግፍንም ይጠጣል።
7በምሳሌ የሚናገር ሞኝ፥
እንደተንጠለጠሉ የአንካሳ እግሮች ነው።
8ለሞኝ ክብርን የሚሰጥ
ድንጋይን በወንጭፍ እንደሚያስር ነው።
9በሞኝ የሚነገር ምሳሌ፥
በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።
10ሞኝን ወይንም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር ሰው ነው፥
ሁሉን እንደሚያቆስል አዳኝ ነው።#26፥10 ሁሉንም እንደሚሠራ ታላቅ ሰው ነው።
11 # 2ጴጥ. 2፥22። ወደ ሞኝነቱ የሚመለስ ሰው፥
ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ነው።
12ለራሱ ጠቢብ የሆነ የሚምስለውን ሰው አየኽውን?
ከእርሱ ይልቅ ሞኝ ተስፋ አለው።
13ሰነፍ ሰው፦ “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ፥
አንበሳ በጎዳናዎች ላይ አለ” ይላል።
14መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፥
እንዲሁ ሰነፍ ሰው በአልጋው ላይ ይገላበጣል።
15ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፥
ወደ አፉም መመለስ ለእርሱ ድካም ነው።
16ሰነፍ ሰው በጥበብ ከሚመልሱ ከሰባት ሰዎች ይልቅ
ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።
17በማይመለከተው ገብቶ የሚሟገት፥
ውሻን በጆሮው እንደሚይዝ ነው።#26፥17 ግሪኩ “ውሻን በጅራቱ እንደሚይዝ ነው” ይላል።
18ትንታግንና ፍላጻን ሞትንም እንደሚወረውር
እንደ ዕብድ ሰው፥
19ባልንጀራውን የሚያታልል፦
“ስቀልድ ነው” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው።
20እንጨት ባለቀ ጊዜ እሳት ይጠፋል፥
ጆሮ ጠቢ በሌለበትም ዘንድ ጠብ ጸጥ ይላል።
21ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንዲያበዛ፥
እንዲሁ ቁጡ ሰው ጠብን ያበዛል።
22የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥
እርሱም እስከ ሆድ ጉርጆች ድረስ ይወርዳል።
23ክፋት በልቡ ሳለ ፍቅርን የሚናገር ከንፈር
በብር ዝገት እንደተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።
24ጠላት በከንፈሩ ተስፋ ይሰጣል፥
በልቡ ግን ተንኰልን ያኖራል።
25በልቡ ሰባት ርኩሰት አለበትና
በቃሉ አሳምሮ ቢናገርህ አትመነው።
26ጠላትነቱን በተንኰል የሚሸሽግ፥
ክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል።
27 # ሲራ. 27፥25-27። ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥
ድንጋይንም የሚያንከባልል ይገለበጥበታል።
28ሐሰተኛ ምላስ ያቈሰላቸውን ሰዎች ይጠላል፥
ልዝብ አፍም ጥፋትን ያመጣል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ